የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የ2.1 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበ

Date:

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ባከናወናቸው ተግባራት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የ2.1 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አስታዉቋል።

ተቋሙ ይህንን ስኬት ያስመዘገበው በመንግሥት እየተተገበረ ባለው የሪፎርም (የለውጥ) ሂደት እና በተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ አማካኝነት መሆኑ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ ( ዶ/ር) እንደገለፁት ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ ቀደም የነበረበትን ከፍተኛ የዕዳ ጫና በመቋቋም እና አሠራሩን በማዘመን ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩ ትልቅ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል።

በተለይም ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተላልፎ የነበረው ከፍተኛ ብድር ተቋሙን ለከፍተኛ ኪሳራ ዳርጎት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን የተገኘው ትርፍ ግን ተቋሙ ካለበት የብድር ጫና ወጥቶ ራሱን እንዲችል መንገድ የሚከፍት መሆኑ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...