የኢትዮጵያ እዳ እና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባ ሳይገኙ ቀሩ

Date:

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እዳ እና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽንን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የፊት ለፊት ግምገማ ላማካሄድ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ለ2:30 ቀጠሮ ይዞ የነበር ቢሆንም፤ የተቋሙን የስራ ኃላፊዎች የመገኘት ግዴታ ቢኖርባቸውም ሳይገኙ ቀርተዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ መለስ መና የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ የቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የቦርድ አባላት በተገኙበት የተቋም አደረጃጀት፣ አሰራር ላይ ግልጽነት የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ፊት ለፊት አስፈላጊ መሆኑ በቋሚ ኮሚቴው በኩል መልእክት እንዲደርስ እና በዚያ ላይ ወይይት ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን አስረድተዋል፡፡

ይሁንና የተቋሙ የስራ ሃላፊዎች እና የቦርድ ተወካዮች በስራ ምክንያት መገኘት እንዳልቻሉ አረጋግጠናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የተቋሙ ኃላፊ እና የቦርዱ ሰብሳቢ በሌሉበት ወይይቱን ማካሄድ ካሰብነው ግብ አንጻር የተሳካ ይሆናል የሚል ግምት ስለሌለን ወይይቱ ወደ ሌላ ቀን ተዘዋውሯል ብለዋል።

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስራ ኃላፊዎችን አስከ 3:20 ድረስ ጠብቆ ውይይቱን በቀጣይ ሁሉም አካላት በተገኙበት ይካሄዳል ሲል አስረድቷል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ስራ አስፈጻሚው በበኩላቸው ተቋሙ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ እንደሆነው አስረድተው የተቋሙን ቁመና ለማስተካካል በሌላ ቀን ዋና የስራ ሃላፊዎችም ሆነ ተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት በተገኙበት ማካሄድ ይሻላል ካሉ በኋላ ስብሰባው ወደ ሌላ ቀን ተዘዋውሯል፡፡

(ሸገር ራዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ፤ አደረሰን

ሰማያት ተከፈቱ ፣ ምስጢርም ተገለጠ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመዷ ቅድስት...

አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር

"አባዬ… ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" ​የአርቲስት...

የአንበሶቹ ትንሳኤ፦ የዳካር እንባ እና የቴራንጋ ድል

​በዳካር ሰማይ ስር ዛሬ ጨረቃ አልወጣችም፤ ይልቁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ...

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...