የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በህዝብ የተያዙ ኩባንያዎች አስፈላጊ ሰነዶችን እና መረጃዎችን እንዲያቀርቡ የተሰጠውን ቀነ-ገደብ ለአንድ ወር ማራዘሙን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ኩባንያዎቹ እስከ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሰነዶችንና መረጃዎችን እንዲያቀርቡ አሳስቦ ነበር። ነገር ግን፣ ከኩባንያዎቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለመቀበል እንዲቻል የጊዜ ገደቡ እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ተራዝሟል።
ይህ ማራዘሚያ አስፈላጊውን መረጃ እስካሁን ላላቀረቡ ኩባንያናት የመጨረሻ እድል እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ባለስልጣኑ ኩባንያናቱ የተራዘመውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም አስፈላጊ ሰነዶችንና መረጃዎችን እንዲያቀርቡ አሳስቧል።
ማራዘሚያው ከ50 በላይ የአክሲዮን ባለቤቶች ያሏቸው እና በአሁኑ ወቅት አክሲዮኖችን ለህዝብ ሽያጭ በማቅረብ ላይ ያሉ ኩባንያዎችን ይመለከታል።
