የ”ካራማራ ድል” የኢትዮጵያውያን የአይበገሬነት ጽናት የታየበት ድል!!

Date:

ከዛሬ 47 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ጦር የሶማሊያን ጦር አሽንፎ ካራማራ ላይ ስንደቅ አላማውን አውለበለበ።

47ኛው የካራማራ ድል መታሰቢያ የሶማሊያ ጦር በምስራቅ በኩል 700 ኪሜ፣በደቡብ በኩል ደግሞ 300 ኪሜ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቶ ነበር


47ኛው የካራማራ ድል መታሰቢያ በዓል ዛሬ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ የወዳጅነት ፓርክ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ ኢትዮጵያውያን በወራሪው የሶማሊያ የዚያድ ባሬ ጦር ያስመዘገቡትን ደማቅ ድል በማሰብ የሚከበር ነው፡፡

“ታላቋን ሶማሊያ” የመገንባት ውጥን ይዞ በ1970 ዓ.ም ምስራቃዊ ኢትዮጵያን የወረረው የዚያድ ባሬ ጦር በጀግና ኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ድባቅ ተመቶ ወደመጣበት መመለሱ ይታወቃል።

ከዛሬ 47 ዓመታት በፊት የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር ድንበር ጥሶ ወደ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ገብቶ የነበረውን የሶማሊያን ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት በማስወጣት ካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ማወለብለቡን ታሪክ ያስታውሳል።

የካራማራ ድል ከደርግ ውድቀት በኋላ በመንግስት ደረጃ የማይከበር ድል ቢሆንም የቀድሞ ሰራዊት አባላትና ግለሰቦች በተነሳሽነት እያከበሩት ነው፤ በዓሉም ብሄራዊ በዓል ሆኖ በመንግስት እንዲከበር በተደጋጋሚ ጥያቄ እየቀረበ ነው። እርስዎስ ምን ይላሉ?

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከባድ ሙስና የተከሰሱትን 4 ተከሳሾችን፤ ፖሊስ ፍርድ ቤት ማቅረብ ሳይችል ቀረ

በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በፖሊስ የ'ይፈለጋሉ" ማስታወቂያ የወጣባቸው...

ስለመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ውጥረት እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች

🔸 ትላንት ምሽት ከኢራን ግዛት የተተኮሰ የሮኬት ጥቃት በሰሜናዊ...

የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕጉ በጋዜጣ እስኪታተም ረቂቅ ሰነዶችን ከመጠቀም እንዲቆጠብ የፍትሕ ሚኒስቴር አሳሰበ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ...

ፔንታጎን የእስራኤል ስለላ እንደሚያሳስበው ተገለጸ

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፔንታጎን እስራኤል ከፍተኛ ልዑኮችን ጨምሮ የአሜሪካ...