የዓለም አቀፍ እርዳታ ቅነሳ የእናቶችን ሞት በመቀነስ የተገኘውን ተስፋ አደጋ ላይ ጥሏል ሲል ተመድ አስጠነቀቀ

Date:

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ኤጀንሲዎች ዛሬ ባወጡት ሪፖርት፣ ከእርግዝና እና ከወሊድ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች የሚሞቱ እናቶች ቁጥር በዓለም አቀፍ ደረጃ በ40 በመቶ ቢቀንስም፣ እየተካሄደ ያለው የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳ ይህን እድገት አደጋ ላይ ጥሏል።

ሪፖርቱ ከ2016 ጀምሮ የእድገቱ ፍጥነት መቀዛቀዙንና በ2023 ብቻ 260,000 የሚገመቱ ሴቶች መሞታቸውን ያሳያል።

በተለይም በሰብአዊ ቀውሶች ውስጥ የሚገኙ ነፍሰ ጡር ሴቶች ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

የተ.መ.ድ ኤጀንሲዎች የእናቶችን ህይወት ለመታደግ የሚያስፈልገውን ድጋፍ በአስቸኳይ እንዲጨምር ጥሪ እያቀረቡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ ከኢራን ጋር የተስማሙባቸውን ነጥቦች ከአርብ በፊት ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማቆም የተስማሙባቸውን...

‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ

(አጭርዳሰሳ) በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) የመጽሐፉርዕስ፡- ሃገረ ትግራይ የመጽሐፉ ዓይነት፡-...

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...