የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሜሪካ እና ቻይና “መካከል እንደማይመርጡ” ተናገሩ

Date:

በቅርቡ ወደ ቤጂንግ ለመጓዝ እየተዘጋጁ ያሉት የዩናይት ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ከአሜሪካ ወይም ከቻይና ጋር ባላቸው ግንኙነት ውስጥ “ከሁለቱ አንዱን ለመምረጥ” እንደማይገደዱ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዩናይትድ ኪንግደም በንግድ፣ ደኅንነት እና መከላከያ ዘርፎች ከአሜሪካ ጋር ያላትን “የቅርብ ግንኙነት” እንደምታስጠብቅ ተናግረዋል። አክለውም ግን “ጭንቅላትህን አሸዋ ውስጥ ቀብረህ ቻይናን ችላ ማለት… ስሜት የሚሰጥ ነገር አይሆንም” ብለዋል።

ስታርመር ከዜና ወኪሉ ብሉምበርግ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ የዓለም ሁለተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ወደሆነችው ቻይና የሚያደርጉት ጉብኝት ለብሪታኒያ ኩባንያዎች “ጉልህ እድሎችን” ሊያስገኝ እንደሚችል ገልጸዋል።

በርካታ የዩናይትድ ኪንግደም የንግድ አመራሮች አብረዋቸው ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ጉብኝት የሚያደርጉት አገራቸው ለንደን ውስጥ አዲስ ሰፊ የቻይና ኤምባሲ ለመገንባት የተያዘውን አከራካሪ እቅድ ባጸደቀች በቀናት ልዩነት ውስጥ ነው።

ለረጅም ጊዜ የተጓተተው ይህ ውሳኔ የተላለፈው ታዋሚዎች የሚገነባው ኤምባሱ የቻይና ሰላዮች ማዕከል ይሆናል የሚል ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ነው።

“ብዙውን ጊዜ በቀላሉ ከአገራት መካከል እንድመርጥ እጋበዛለሁ። ይህንን አታድርጉ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

“አስታውሳለሁ ከአሜሪካ ጋር የንግድ ስምምነት ስፈጽም ሁሉም ሰው ከአሜሪካ እና አውሮፓ መካካል መምረጥ እንዳለብኝ ይነግረኝ ነበር። ‘ይህንን ምርጫ አላደርግ” ብያቸዋለሁ” ሲሉ በቃለ መጠይቁ ተናግረዋል።

“ከአሜሪካ ጋር በጣም ቅርብ ግንኙነት አለን፤ በእርግጥም እንገልገዋለን። ከደኅንነት እና መከላከያ ጎን ለጎን ያልንን ንግድ እናስጠብቃለን” በማለት አክለዋል

“በእኩል ደረጃ፤ የዓለም ሁለተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ ሆና እያለ ችና የንግድ እድሎች እያሉ ጭንቅላትህን አሸዋ ውስጥ መቅበር እና ቻይናን ችላ ማለት ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም” ሲሉም አቋማቸው ገልጸዋል።

BBC Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...