የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ በሰጠችው እውቅና ላይ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

Date:

​ስብሰባው ለነገ መርሃ ግብር ተይዞለታል ሲሉ በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ዳኒ ዳኖን አስታውቀዋል።

​እስራኤል ባለፈው ሐሙስ ለሶማሊላንድ በይፋ እውቅና የሰጠች ሲሆን፣ ይህም እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ ከሶማሊያ ተገንጥላ ራሷን በራሷ ለምታስተዳድረው ሱማሌላንድ እውቅና የሰጠች በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር አድርጓታል።

​ይህ የእስራኤል እርምጃ ሰፊ ዓለም አቀፍ ምላሾችን አስከትሏል።

ሶማሊያ እውቅናውን በሉዓላዊነቷ ላይ የተፈጸመ “ሆን ተብሎ የተደረገ ጥቃት” ስትል በፅኑ አውግዛለች።

በተጨማሪም እንደ ባሕረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት፣ የእስልምና ትብብር ድርጅት፣ የአፍሪካ ሕብረት እና የአውሮፓ ሕብረት ያሉ ዋና ዋና ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት በእስራኤል አካሄድ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መልካም አዲስ ዓመት!!

  ግዮን መጽሔት :-   አዲሱን የኢትዮጵያ ዓመት ስንቀበል፣ ለውዷ ኢትዮጵያችንና...

የድሬዳዋ አስተዳደር ተሿሚዎች

4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደዉ...

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተሿሚዎች

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ...

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ተሿሚዎች

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ...