የ12ኛ ክፍል የሪሚዲያል መርሃ ግብር መቁረጫ ነጥብ ተወሰነ

Date:

ለ2019 ዓ.ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ ተወስኗል ሲል ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸው ተገልጿል። የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ደግሞ ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ብቁ ናቸው ተብሏል፡፡

በልዩ ድጋፍ የሚታዩ ተማሪዎች መቁረጫ ነጥብን በተመለከተ ሚኒስቴሩ ይፋ ባደረገው መረጃ ደግሞ ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ወንድና ሴት ተማሪዎች፣ ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ለሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይ ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ተማሪዎች ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ ወጤት ያስመዘገቡ መስፈርቱን እንደሚያሟሉ ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

እንዲሁም በተፈጥሮ ወይም በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ እና በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውር ወንድና ሴት ተማሪዎች ደግሞ ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ ማስመዝገብ የቻሉ ለሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ ናቸው ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መልካም አዲስ ዓመት!!

  ግዮን መጽሔት :-   አዲሱን የኢትዮጵያ ዓመት ስንቀበል፣ ለውዷ ኢትዮጵያችንና...

የድሬዳዋ አስተዳደር ተሿሚዎች

4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደዉ...

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተሿሚዎች

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ...

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ተሿሚዎች

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ...