የሊጉ መሪ አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 4ለ0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።
የአርሰናልን ግቦች ዙቢሜንዲ ፤ ቪክቶር ዮኬሬሽ ፤ ጋብሬል ጄሱስ እና ዳርሎው በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሯል። ጋብሬል ጄሱስ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ሶስት ግቦችን አስቆጥሯል።
ቼልሲ ዌስትሀም ዩናይትድን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸነፍ።
ዌስትሀም ዩናይትድ በጃሮድ ቦውን እና ሰመርቪሌ ሁለት ግቦች ጨዋታውን 2ለ0 ሲመራ ቢቆይም ጇ ፔድሮ ፤ ማርክ ኩኩሬላ እና ኢንዞ ፈርናንዴዘ ከእረፍት በኋላ ባስቆጠሯቸው ሶስት ግቦች ቼልሲ አሸንፎ ወጥቷል።
በአሰልጣኝ ሊያም ሮሴንየር የሚመራው ቼልሲ አምስተኛ ተከታታይ ድሉን ማሳካት ችሏል።
ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደርገውን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ሁጎ ኤኪቲኬ ሁለት ፣ ፍሎሪያን ቨርትዝ እና ኮናቴ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ሊቨርፑል ከአምስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በኋላ ሶስት ነጥብ አሳክቷል።
ፍሎሪያን ቨርትዝ ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች ስድስት የግብ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።
በሌሎች ጨዋታዎች በርንማውዝ ዎልቭስን 2ለ0 ሲያሸንፍ ኤቨርተን ከብራይተን 1ለ1 ተለያይተዋል።
