የ60 ሚሊዮን ብር የዲጂታል ሎተሪ ባለዕድለኞች ሽልማታቸውን ተረከቡ

Date:

በኢትዮጵያ የሎተሪ ታሪክ ውስጥ ግዙፍ የተባለውን 60 ሚሊዮን ብር ጨምሮ የሌሎች ከፍተኛ ሽልማቶች የዕጣ አወጣጥ እና የሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት በስካይላይት ሆቴል በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል።

👉 አቶ ብርሃኑ ጎበዜ (ከባሌ ጎባ ከተማ) የ60 ሚሊዮን ብር አሸናፊ
👉 አቶ ማስረሻ መላኩ (ከአዲስ አበባ) የ20 ሚሊዮን ብር አሸናፊ
👉 አቶ ብዙነህ ታደሠ (ከቢሾፍቱ ከተማ) የ10 ሚሊዮን ብር አሸናፊ

በተጨማሪም 12 ዕድለኞች እያንዳንዳቸው የ1 ሚሊዮን ብር ባለቤት ሆነዋል።

ባለፉት ሦስት ወራት ከጥቅምት 9 እስከ ጥር 9 በቆየው በዚህ የዲጂታል ሎተሪ መርሃ-ግብር ላይ ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በኢትዮ ሎተሪ ድረ-ገጽ፣ በቴሌ ብር፣ በ8989 አጭር የፅሁፍ መልዕክት (SMS) እና በባንኮች አማካኝነት በቤታቸው ሆነው ዕድላቸውን ሲሞክሩ ቆይተዋል።

በዚህ መርሃ-ግብር ለአሸናፊዎች ከተበረከተው ገንዘብ ባሻገር የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን በመተባበር ለሶስት መንግስታዊ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ አበርክተዋል።

በዚህም መሰረት፡
📍 ለባሌ ሮቤ ከተማ አቅመ ደካሞች የጤና መድህን 1.8 ሚሊዮን ብር፣
📍 ለአዲስ አበባ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ 2 ሚሊዮን ብር፣
📍 ለአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን 2.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ የዲጂታል ሽግግር፣ ደህንነቱና ግልፅነቱ የተጠበቀ ዘመናዊ አሰራር መሆኑን በተግባር አሳይቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...