ዩ ኤስ ኤ አይ ዲን ወደ ነበረበት እንዲመለስ ፍርድ ቤት ወሰነ

Date:

አንድ የአሜሪካ ፌደራል ፍርድ ቤት፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር የአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅትን (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲን) ወደነበረበት እንዲመልስ ትዕዛዝ መስጠቱን ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ፍርድ ቤቱ፣ ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ በጥድፊያ እንዲፈርስ የተደረገበት መንገድ የአሜሪካ ሕገመንግሥቱን በብዙ መንገድ ጥሷል ሊባል የሚችል ነው ማለቱን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ዩ ኤስ ኤ አይ ዲን የማፈረስ ወይም መልሶ የማዋቀር ሥልጣን የሕግ አውጭው ምክር ቤት ብቻ ሥልጣን እንደኾነ ፍርድ ቤቱ ጠቅሷል ተብሏል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ ከድርጅቱ 83 በመቶ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ እንደታጠፉና ቀሪዎቹ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ሥር መጠቃለላቸውን ከሳምንት በፊት መግለጣቸው አይዘነጋም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዝዳንት...

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካ ” American Space ” ማዕከል ተመረቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመውን "American...

አሐዱ ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ

አሐዱ ባንክ ሥራ የጀመረበትን 4ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ኩነቶችን...

ዕንባ ጠባቂ ከቀረቡለት አቤቱታዎች 84% በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት...