ደራሲ አሌክስ #በሐበሻ_ደም መፅሐፍ መጥቷል !

Date:

ደራሲ አለማየሁ ታዬ – አባዳገት !

የሚስኪኖች ደራሽ አሌክስን
መፅሐፉን በጋራ በማሳተም እናግዘው !

ደራሲ አለማየሁ ታዬ – ገደአታ – ኡኑሹ ይባላል።

ቂርቆስ | ጨርቆስ ሰፈር ነው ተወልዶ ያደገው።

አሌክስ ከዚህ በፊት ፦

የጨርቆስልጅ ፣ #ፍለጋ እና #የወንዶችገዳም

የተሰኙ መፅሐፎችን አበርክቶልናል።

አሁን ደግሞ #የሐበሻ_ደም የተሰኘ አጫጭር
መጣጥፎችንና የሐበሻን ዘረመል የሚያጠና
ጥናታዊ ፅሑፍ ያካተተ አራተኛ መፅሐፉን
ሊያደርሰን በዝግጅት ላይ እያለ ፦

የሕትመት ዋጋ መጨመር እንቅፋት ሆኖበታል።
600,000.00 ( ስድስት መቶ ሺህ ብር )
ለማሳተሚያ የተጠየቀው ብር ነው።

አሌክስ ስለቂርቆስ | ጨርቆስ ተናግሮ አይጠግብም።
በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ እየተጋበዘ በጣፋጭ
አንደበቱ ስለቂርቆስ | ጨርቆስ በቂ ግንዛቤ
አስጨብጧል።

የቂርቆስን | ጨርቆስን ታሪክ ከእግር እስከራሱ
ፈትፍቶ አስረድቷል። የጨርቆስ ልጅ ብሎ ፅፎም
በመፅሐፍ አሳትሞ የሰፈሩን ስም ከፍ ያደረገ
ደራሲ ነው።

አሌክስ በታይላንድና ዱባይ ሰርቶ ፣ እንዲሁም
ራይድ ሰርቶ ባፈራው ጥሪት ሆቴል ከፍቶ ነበር።
ሆቴሉ በኪሳራ ምክንያት ተዘግቶበት ነው እንጂ
ይኼንን አራተኛ መፅሐፉን ራሱ ማሳተም ይችል
ነበር።

ህፃናትን እና አረጋዊያንን የሚደግፍ ፣ ስደትን
ለማስቀረት የሚጥር ፣ ወጣቱ ከአልባሌ ቦታ
ርቆ ወደስፖርት ማዘውተሪያ እንዲውሉ የሚያደርግ ፣
አንባቢ ትውልድ እንዲፈራ ላይብረሪ እንዲሰራ
የሚጥር የቂርቆስ | ጨርቆስ ሰፈር መኩሪያ ነው።

በቅጠል ለሚጠቀሙ እናቶች ከወዳጆቹ ጋር
በመተባበር የኤሌክትሪክ ምጣድ አበርክቷል።

አሌክስ ማህበራዊ ህይወት ላይ ግንባር ቀደም
ተሳታፊ ነው።

የቂርቆስ | ጨርቆስ ሰፈር መረዳጃ ዕድር መስራች ነው።
አራዳና ጨዋታ አዋቂም ነው።

የቂርቆስ ተወላጅ ባለሃብቶች ፦
የጃምቦ ሪል ስቴት ባለቤት ፦ አቶ ደበበ
የሰንሻይን ኮንስትራክሽን ባለቤት ፦ አቶ ሳሙኤል ታፈሰ
ባለሃብት ፦ አቶ ግርማ ገላው

ተወልዳችሁ ያደጋችሁበትን ቂርቆስ | ጨርቆስ ሰፈር
ታሪክ እየጻፈ የሚያደርሰውን ወንድማችሁን ደግፉት !

ቂርቆስ | ጨርቆስ ተወልዳችሁ ያደጋችሁ አርቲስቶች
ስለእናንተ በየሄደበት በኩራት ስለሚናገርላችሁ ፣
ስለእናንተ ተናግሮ ስለማይጠግበው ወንድማችሁ
አሌክስን ደግፉት !

የቂርቆስ ሰፈር ተወላጅ ዳያስፖራዎች
ወንድማችሁን ደግፉት !

በጠራችሁት ቦታ አክብሮ ቃለ – ምልልስ የሚሰጣችሁ
ሚዲያዎችም ቢያንስ ሰዎች ጋር በማዳረስ አግዙት !

ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖችም አሌክስ አራተኛ
መፅሐፉን እንዲያደርሰን የቻላችሁትን ደግፉት !

የአሌክስን መፅሐፍ ለማሳተም መደገፍ የምትፈልጉ ፦
1000610024983
CBE
ዓለማየሁ ታዬ ለማ
TeleBirr – 0911-90-55-92
Alemayehu Taye

በብር መርዳት የማትችሉ ቅን ኢትዮጵያዎች እና
የቂርቆስ | ጨርቆስ ባለሃብቶች ጋር እንዲደርስለት
Share ሼር አድርጉት 🙏

Alemayehu Taye አሌክስ ያሰብከውን ያሳካልህ !
መልካሙ ሁሉ ይግጠምህ !

አክባሪህና አድናቂህ
ዘሪሁን ተዝናኑ
ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...