በBRICS ቡድን መስራቾች ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተመሰረተው NDB በአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም ደቡብ አፍሪካ ላሉት ዋና ዋና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ምንጭ በፍጥነት የሚያገኙበት አማራጭ ይዞ ብቅ ማለቱ ተሰማ።
በምዕራባውያን ኃያላን ሀገራት ከመጠን በላይ የሆነ የበላይነት ለመታገል እ.ኤ.አ. በ2009 የተቋቋመውና
እንደ የዓለም ባንክ፣ የሰባት ሃያላን ቡድን ሀገራት (G7) እና የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ባሉ ዋና ዋና የባለብዙ ወገን ተቋማት ሀገራት የምዕራቡ ዓለም ጥገኛ እንዲሆኑ አድርጓል ሲል የሚደመጠው BRICS ደቡብ አፍሪካ ለመገንባት ላሰበቻቸዉ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ብድር መፍቀዱን ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ዘግቧል ።
በደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ መንገዶች ኤጀንሲ (SANRAL) በጆሃንስበርግ የብድር ስምምነቱ ሲፈረም እንደገለፀው ከሆነ ብድሩ ወሳኝ የትራንስፖርት መስመሮችን ለማሻሻል፣ ግንኙነትን ለማሻሻል፣ መጨናነቅን በመቀነስ እና በወሳኝ የኢኮኖሚ ኮሪደሮች ላይ ደህንነትን ወደ ማሳደግ እንደሚዉል ገልጿል ።
የSANRAL ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሬጂናልድ ዴማና እንደተናገሩት ብድሩ በደቡብ አፍሪካ የግንባታ እና የትራንስፖርት ዘርፎች በጣም አስፈላጊ የሆነውን ካፒታል ያስገባል ። እንዲሁም የተቀላጠፈ የሸቀጦች እና የሰዎች ዝውውርን በማስቻል የስራ እድል ፈጠራን የሚደግፍ እና የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን ለማነቃቃት ያስችላል ብለዋል።
ኤጀንሲው በበኩለ ይህ ብድር በደቡብ አፍሪካ ከታየዉ ካለዉ የዓመታት ዝቅተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎት በኋላ እየጨመረ የመጣውን የትራንስፖርት ፍላጎት ለማሟላት ከሚደረገው ጥረት አንዱ አካል መሆኑን ጠቁሟል።
እንደሚታወቀው በባለብዙ ወገን ተቋማት ውስጥ በማደግ ላይ ያሉ የኢኮኖሚ አመለካከቶችን አንድ ግንባር ለመፍጠር ሙከራዎች እያደረገ የሚገኘውና 40% በላይ የአለም ኢኮኖሚ እና ከአለም ህዝብ ግማሽ ያህሉን ያቀፉ ሀገራችን በዉስጡ የያዘዉ BRICS እ.ኤ.አ. በ 2023 BRICS የመሪዎች ስብሰባ ላይ ግብፅና ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ሀገራትን ወደ ቡድኑ የቀላቀለ ሲሆን በ2024 ባደረገው የመሪዎች ጉባኤ ላይም ቤላሩስ፣ ቦሊቪያ፣ ኩባ፣ ካዛኪስታን፣ ማሌዥያ፣ ናይጄሪያ፣ ታይላንድ፣ ኡጋንዳ እና ኡዝቤኪስታን “የአጋር አገሮች” ምደባ በመቀላቀል ተደራሽኘቱን እያሰፋ ይገኛል ።
ህብረቱ የአባላቱን ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ፖሊሲዎች ለማስተባበር ፣ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማትን ለማግኘት እና በአሜሪካ ዶላር ላይ ጥገኝነትን ለመቀነስ እየሞከረ እንደሚገኝ በህብረቱ ድህረገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።
የኔታ ቲዩብ
