ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) በኬንያ ሞምባሳ ከተማ አቅንቶ ከ አቦጊዳ ባንድ ጋር የሙዚቃ ስራውን ሊያቀርብ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ኮንሰርቱ የሚከናወነው አርብ የካቲት 6 እስከ ሰኞ 9 ድረስ ለሶስት ቀናት ያክል ያቀርባል፡፡
በ’ሪፍ’ ሆቴል ሞምባሳ የሚደረገው የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የሙዚቃ ድግስ ለተከታታይ ቀናት በአንድ ቦታ የሚደረግ መሆኑ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሙዚቃ ዝግጅቶች ልዩ ያደርገዋል።
ከዚህ ቀደም ድምፃዊው ከአቡጊዳ ባንድ ጋር በመሆን በዋሽንግተን ዲሲ፣ ስቶኮልም ፣ ፍራንክፈርት፣ሲያትል፣አትላንታ፣እስራኤል የተለያዩ ሀገራት በመዘዋወር የሙዚቃ ኮንሰርት ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
