ድንቁ ቅፅበት ለወመዘክር ተበረከተ

Date:

ደራሲ(አጋዝ) ገብረየሱስ ኃይለማሪያም ያነሷቸው ”የሚሊኒየሙ መሸኛና መቀበያ” ፎቶግራፎችን ጨምሮ ጥንታዊ መፅሐፍቶቻቸውን ለወመዘክር አበረከቱ።

‘ድንቁን ቅፅበት’ በሚል የደራሲ ገብረየሱስ ኃይለማርያም በፈረንጆቹ ሚሊኒየም መባቻ እስከ ወጨጫ ተራራ በመጓዝ ያነሷቸው የሚሊኒየሙ ጀንበር መሸኛና መቀበያ ፎቶግራፎችን ጨምሮ የጫሙት ሽካ፣ ተኬትነት አጂነት/አገኪ፣ ነሁቸርና The Gurage and their Culture የተሰኙ የድርሰት ሥራዎቻቸውን ለብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አስረክበዋል።

በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበረሰብ ልማት ዘርፎች ያበረከቷቸው የሕይወት ዘመን አገልግሎቶች “አጋዝ” የሚል ባህላዊ ስያሜ የተሰጣቸው አጋዝ ገብረኢየሱስ ኃይለማርያም በጉራግኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ 16 መጽሐፍትን ጽፈዋል። ለጉራጌ ባህልና ቋንቋ ልማት ካበረከቱት አስተዋጽኦ ባሻገር የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅትን (ጉህራልድ) መሥርተዋል፤ አገልግለዋልም። በሌሎች ሀገራዊና ዓለምአቀፍ ተቋማትም አሻራቸውን አኑረዋል።

ተወዳጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ከሶዶ ለማ ሚድያ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ በወመዘክር ኅሩይ አዳራሽ ነው የተካሄደው።

በዚህም ታላላቅ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበትም የደራሲው ተወዳጅ መጻሕፍትና ያነሷቸው ታሪካዊ ፎቷግራፎች ለታሪካዊው ወመዘክር ተበርክቷል።

”ድንቁ ቅፅበት” መርሀ ግብር በምርቃት የተጀመረ ሲሆን ደራሲ በብርሃነ ዓለሙ በአጋዝ ገብረየሱሰ መፅሀፍና የአፃፃፍ ስልት ላይ እንዲሁም ገጣሚ ክፍሌ ተመስገን ከጫሙት ሽካ መፅሐፍ የተቀነጨበ ታሪክ አቅርበዋል።

የብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተ መፅሀፍት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ኅላፊ አቶ አባተ ካሣው ሰነዶቹን ሲረከቡ ባደረጉት ንግግር ባለ ታሪኩ አጋዝ ገብረየሱስ ታሪካዊ ሰነዶችን በማስረከባቸው የተሰማንን ልባዊ ደስታ እንገልፃለን ብለዋል።ለደራሲ ገብረየሱስም ከወመዘክር የተዘጋጀ የእውቅናና ምስጋና የምስክር ወረቀት ሰርተፊኬት ሰጥተዋል።

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሠረት አመርጋ በበኩላቸው እንዲህ አይነት ታሪካዊ ስራዎች በሰነድነት ታስበው የርክክብ ሥነ ሥርዓቱ መዘጋጀቱ ለሀገር ትልቅ ነገር ነው ብለዋል። ባህል፣ ቋንቋና ስነ-ፅሑፍን ለትውልድ ከማሸጋገር አንፃር ሚናቸው ትልቅ ነው ያሉት ሀላፊዋ ደራሲው እንደ ሀገር ላበረከቷቸው ታሪካዊ ሰነዶችም ምስጋና አቅርበዋል።

ደራሲ አጋዝ ገብረየሱስ ሀይለማርያም በበኩላቸው ስራዎቹን ሳከናውን እዚህ ይደርሳል ብዬ ባይሆንም የበርካታ ታሪክና ባለታሪኮች ሰነድ መገኛ የሆነው ወመዘክ ፎቶግራፎቼንና የድርሰት ስራዎቼን በአሻራነት መሰነድ በመቻሉ ደስታ ተሰምቶኛል፤ አመሰግናለሁ”ም ብለዋል። ወደፊትም የታሪካዊ ሰነድ ባለቤቶች ስራዎቻቸው ለትውልድ ተደራሽ እንዲሆኑ ለወመዘክር ማስረከብ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ደራሲው ”ድንቁ ቅፅበት” በሚል መርሃ-ግብሩን ላዘጋጁት ተወዳጅ ሚዲያና ሶዶ ለማ ሚዲያም ልዩ ምስጋና አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...