ዶናልድ ትራምፕ በካናዳ ምርቶች ላይ የ100 በመቶ ታሪፍ እንደሚጥሉ ዛቱ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካናዳ ከቻይና ጋር የጀመረችውን አዲስ የንግድ ስምምነት የምትቀጥል ከሆነ በሁሉም የካናዳ ምርቶች ላይ አስቸኳይ የ100 በመቶ ታሪፍ እንደሚጥሉ አስጠነቀቁ።

ፕሬዝዳንቱ የካናዳውን ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒን በፅኑ የኮነኑ ሲሆን ካናዳ ወደ አሜሪካ ገበያ ለሚገቡ የቻይና ምርቶች እንደ ማራገፊያ ወደብ ወይም “drop-off port” እያገለገለች ነው ሲሉ ከሰዋል። ትራምፕ አክለውም ካናዳ በዚህ አካሄዷ ከቀጠለች ቻይና ሀገሪቱን “በቁሟ ትበላታለች” ሲሉ አስደንጋጭ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ይህ ከፍተኛ ውጥረት የተቀሰቀሰው ካናዳ ቀደም ሲል በቻይና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥላው የነበረውን የ100 በመቶ ታሪፍ ወደ 6.1 በመቶ ዝቅ ለማድረግ በመስማማቷ ነው። ይህ ስምምነት የተደረገው ቻይና በበኩሏ በካናዳ የካኖላ ምርቶች ላይ የጣለችውን ቀረጥ እንድታነሳ በተደረገ ልውውጥ እንደሆነ ታውቋል።

ውጥረቱ ይበልጥ የገነፈለው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ በዳቮስ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር የታላላቅ ሀገራትን ፍጥጫ እና ታሪፍን እንደ ጦር መሣሪያ መጠቀምን መተቸታቸውን ተከትሎ ነው።

የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ትራምፕ የዛቱት የ100 በመቶ ታሪፍ ተግባራዊ ከሆነ የካናዳን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ክፉኛ እንደሚጎዳና የሰሜን አሜሪካን የንግድ ሰንሰለት እንደሚያናጋ እያሳሰቡ ይገኛሉ። በተለይም የአውቶሞቢል ማምረቻ፣ የብረት እና የማዕድን ዘርፎች ለከፍተኛ አደጋ ይጋለጣሉ ተብሏል።

የካናዳ የንግድ ሚኒስትር ዶሚኒክ ሌብላንክ በበኩላቸው ኦታዋ ከቻይና ጋር ሙሉ የነፃ ንግድ ስምምነት ለማድረግ ፍላጎት እንደሌላትና ስምምነቱ የተወሰኑ የንግድ እንቅፋቶችን ለመፍታት ብቻ የታለመ መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩን ለማርገብ ሞክረዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከፍተኛ የታሪፍ መጠኖችን እንደ ድርድር መሣሪያ መጠቀማቸው በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ አለመረጋጋት የፈጠረ ሲሆን ከዚህ ቀደም በአውሮፓ አጋሮቻቸው ላይ መሰል ማስጠንቀቂያዎችን ሰጥተው በኋላ ላይ ማፈግፈጋቸው ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...