ጀግናውና ጀግኖችን ቀራፂው የኦጋዴኑ በረሃ ቁጡ ነብር!!!….ኮሎኔል ዘመዱ ኃይሌ ተሸለሙ

Date:

ጀግናው እና ምንግዜም እናት ኢትዮጵያን ባዩ… አዛውንቱ ኮሎኔል ዘመዱ ኃይሌ የተሸለሙት ፤ ለእናት ሃገር ኢትዮጵያ አንድነት፣ ክብርና ነፃነት! ብሎም ለዜጎቿ ዕኩልነት ፣ ለዳር ድንበሯ መከበርና ለሉዓላዊነቷ ሲሉ ፤ ከአፍላ ወጣትነታቸው ዕድሜ ጀምሮ እስከ ጎልማሳነታቸው ዘመን ማክተሚያ ድረስ በቅንነትና በታማኝነት፣ ልዩ! በሆነ የእናት ሃገር ፍቅርና ከፍተኛ የወገን ወዳድነት ስሜት! ከሞት ባሻገር ያለውን ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ሁሉ ተጋፍጠው! እጅግ በሚያኮራ የጀግንነት ተግባሮች ኢትዮጵያን ያገለገሉ ታላቅ የጦር መሪና ዓርአያነታቸው ጉልህ የሆነ ባለውለታ የሃገር ልጅ በመሆናቸው ነው። 💚💛❤

🔵 ➡️ ጀግናውን የሃገርና የትውልድ ባለውለታ ኮሎኔል ዘመዱ ኃይሌን እጅግ የተከበሩ የሴት ባለሙያና ጥንቁቅ ወታደር የሆኑት ባለቤታቸው ወይዘሮ አልጋነሽ ከበደ ፣ ቤተሰቦቻው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በጣም ደማቅ በነበረ ሥነ-ሥርዓት የሸለሟቸው፦ በአዲስ አበባ ከተማ የጉርድ ሾላ ፣ መሳለሚያና ኮተቤ አካባቢ ማኅበረሰብ የወዳጅነት ሕብረት አባላት የሆኑ ወጣቶች ናቸው።

🔵➡️ ዕሁድ ጥር 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ጉርድ ሾላ በሚገኘው የገዳመ ሲታውያን ማርያም ጽዮን ካቶሊክ ሚሽን ፩ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጽር ግቢ ውስጥ በተካሄደው የኮተቤ መሳለሚያ – ጉርድ ሾላና አካባቢው ማኅበረሰብ የወዳጅነት ሕብረት ፫ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ላይ ፤ ስለ ጀግንነታቸው፣ ስለ ዕውቅ የጦር መሪነታቸው ፣ ስለ ሃገርና ስለ ትውልድ ባለውለታነታቸው ክብር ሲባል… የዋንጫ ሽልማት የተበረከተላቸው ኮሎኔል ዘመዱ ኃይሌ ፤ በዕውነቱ ሽልማቱ የሚገባቸው ታላቅ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ቅንጣት የሚያጠራጥር አይደለም።

🔵 ➡️ ➡️ በመሆኑም ኢትዮጵያዊውን ጀግናና ጀግኖችን ቀራፂ የነበሩትን ኮሎኔል ዘመዱን የሸለሙትን አሰተዋይ የኢትዮጵያን ድንቅ ልጆች ማመስገን የተገባ ነውና… በበኩሌ ሸለሚዎቹንና ጀግናችንን ኮሎኔል ዘመዱን ያከበሩልንን በሙሉ ከ1983 ዓ.ም በፊት በነበረው የኢትዮጵያ ሠራዊት ስም ለማመስገን እወዳለሁ።


🔵 ጥበቡ የማይመረመር ኃያል እግዚአብሔር የመልካም አሳቢነታችሁን ዋጋ በዕጥፍ ድርብ ይክፈላችሁ!!!

👉 እንደገና በዚሁ 2018 ዓ.ም እጅግ በጣም ደስስስ… ብሎኛል። እግዚአብሔር ይመስገን!!!

👉 ለደስታዬ ምክንያት ለሆነው እና ለሳቅ ምንጩ ብዕረኛ በኃይሉ ገብረ-እግዚአብሔር ያለኝ አክብሮት ከልብ ነው። በኃይሉን ቸሩ መድኃኒዓለም የጤና ባለጸጋም ያድርግልኝ።

👉 በኮሎኔል ዘመዱ ኃይሌ የክብር ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ በመታደሜ ከፍተኛ የመንፈስ ዕርካታ ነው ያገኘሁት።

🔵 ደግሞም ያ ለኮሎኔል ዘመዱ ኃይሌ በፍቅር! በአክብሮት!…. የተበረከተው ሽልማት ለእኔም የተሰጠ ስለመሆኑ በፍፁም አልተጠራጠርኩም።
ወገኖቼ ክበሩልኝ!!!! 💚💛❤

በሰሎሞን ለማ ገመቹ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...