የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ ባንኮች የተከፈለ ካፒታላቸውን በ2018 ዓ.ም ወደ 5 ቢሊየን ብር እንዲያሳድጉ መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ ነው ባንኩ ካፒታሉን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የገለፀው።
ባንኩ ይህን የገለጸዉ የሁለት አመት የስራ አፈፃፀም አራተኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ባካሄደበት ወቅት ነዉ።
በጉባኤው ከባለ አክሲዮኖች የባንኩ አሁናዊ አቅም ምን እንደሚመስል ተጠይቋል፡፡
በመድረኩ ሪፖርቱን ያቀረቡት የባንኩ ስራ አስኪያጅ ሁሴን ሀሰን እንደገለፁት፥አሁን ላይ ያለው የባንኩ አጠቃላይ ሃብት 10 ቢሊየን ብር መድረሱን እና ከ4መቶ44 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ባቀረበው የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንዳመላከተው፥በበጀት ዓመቱ የተገኘው ትርፍ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ3መቶ39.3 በመቶ ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል ብለዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ የተተገበረው የገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን እና የፋይናንስ ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት መደረግ ጫና ፈጥሮበት እንደነበረ ባንኩ አስታዉቋል፡፡
በተጨማሪም ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች እንደነበሩም አያይዘዉ ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ተደራሽነቱን ለማስፋት በበጀት ዓመቱ በከፈታቸው 15 አዳዲስ ቅርንጫፎች አማካይነት አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ቁጥር 100 አድርሷል።
ገዳ ባንክ በቀጣይ የውጭ ባንኮች መግባት የሚፈጥረውን ውድድር ለመቋቋም በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በሰው ኃይል ልማት እና ዘመናዊ የባንክ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ በጉባኤው ላይ ተጠቁሟል።
