ግሎሪ ፋውንዴሽን በ3.5 ቢሊየን ብር የሚገነባ ግዙፍ የትምህርት ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

Date:

ግሎሪ የተቀናጀ ልማት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ በ8 ክልሎች ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት የፕሮጀክት ማብሰሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል።

ፋውንዴሽኑ ለዚሁ ሀገራዊ ፕሮጀክት አርቲስት ደሳለኝ ኃይሉን የክብር ብራንድ አምባሳደር አድርጎ የሾመ ሲሆን፣ የመጀመሪያው የአዳሪ ት/ቤት ግንባታውንም በጎንደር ከተማ እንደሚጀመር አስታውቋል።

“ጥራት ያለው ትምህርት ለአገር እድገት” በሚል መሪ ቃል የተመሰረተው ይህ ፋውንዴሽን፣ በጎንደር ለሚገነባው ተቋም 75 ሺህ ሔክታር መሬት ከከተማ አስተዳደሩ የተረከበ ሲሆን፣ አጠቃላይ ግንባታውን መቶ በመቶ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ከ3.5 ቢሊየን ብር በላይ በጀት እንደሚያስፈልገው ገልጿል።

የፋውንዴሽኑ መስራች ወይዘሮ አስማሩ በሪሁን እንደተናገሩት ፡ በተለያዩ ሀገራት ተጉዘው ያዩት የትምህርት ትኩረትና የአዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚያስመዘግቡት ከፍተኛ ውጤት ተቋሙን ከባለቤታቸው ጋር እንዲመሰርቱ እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል።

ተቋሙ በተለይ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ጎበዝ ተማሪዎችን የምግብና የመኝታ ወጪ ሸፍኖ ጥራት ያለው ትምህርት በነፃ በመስጠት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡትን ተማሪዎች ቁጥር የማሳደግ ራዕይ ሰንቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ለወጣቶች ተግባር ተኮር የሙያ ስልጠና መስጠት፣ በተለይ ሴቶች ላይ በማተኮር ለማኅበረሰብ አቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን መስጠት የፋውንዴሽኑ ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸው በመርሐ ግብሩ ላይ ተብራርቷል።

የተቋሙ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ አለሙ ታፈረ በበኩላቸው፣ ፋውንዴሽኑ ለሀገሪቱ ወጣቶች የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋጽኦ ገልጸው፣ ለዚህ ሀገራዊ ፕሮጀክት ስኬት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የፋውንዴሽኑ ብራንድ አምባሳደር እንዲሆን የተሾመው አርቲስት ደሳለኝ ኃይሉ በንግግሩ ትውልድን ለመገንባት ለተቋቋመው ለዚህ ፋውንዴሽን የቻለውን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጾአል።

ግሎሪ የተቀናጀ ልማት ፋውንዴሽን በኢፌዴሪ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የተመዘገበ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።

(አሐዱ ራድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...