ጎብኚዎች ስለኢትዮጵያ መዳረሻዎች መረጃ የሚያገኙበትና ግብይት የሚፈፅሙበት መተግበርያ መልማቱ ተገለፀ

Date:

ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ  የኢትዮጵያን ቱሪዝም ምርትና አገልግሎት የሚያስተዋወቅ ‘ቪዚት ኢትዮጵያ’ የተሰኘ የግብይት መተግበሪያ ይፋ ሆኗል።

መተግበሪያው በዘርፉ ያሉ ተዋንያንን አንድ ላይ የሚያገናኝ ሲሆን መረጃ ላይ የተመሰረተ ግብይት ተግባራዊ በማድረግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል እንደሆነ ነው የተመላከተው።

ከዚህ ባሻገር ቱሪስቱ ያለውን ግብረመልስ ለመቀበል የሚያስችል ፤ በርካታ ሆቴሎች የዋጋ ቁርጣቸውን የሚያቀርቡበትና የአስጎብጂ ድርጅቶች የጉዞ ጥቅሎች የሚገኝበት እንደሆነ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል።

አክለውም ጎብኚዎች ይዘው ለሚመጧቸው ዕቃዎች ከጉምሩክ ኮሚሽን አስቀድመው ፍቃድ ማግኘት የሚችሉበት መሆኑን አስረድተዋል።

ሀገሪቱ ያላትን የቱሪዝም አቅም ለመጠቀም የዲጂታል መሰረተ ልማት አስፈላጊነት ሌላው አፅንዖት የተሰጠበት ጉዳይ ነው።

መተግበሪያው ላይ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪዎች የተመዘገቡ ሲሆን በቀጣይ ሁሉም የቱሪዝም እሴት ሰንሰለት ተዋንያን በዚሁ ‘ፕላትፎርም’ ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል ተብሏል፡፡

መተግበሪያውን የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደርና የቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ አልምተውታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዝዳንት...

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካ ” American Space ” ማዕከል ተመረቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመውን "American...

አሐዱ ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ

አሐዱ ባንክ ሥራ የጀመረበትን 4ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ኩነቶችን...

ዕንባ ጠባቂ ከቀረቡለት አቤቱታዎች 84% በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት...