ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጅቡቲ እና የሶማሊያ መሪዎችን በጅግጅጋ ተቀበሉ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ዑመር ጌሌን እና የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድን በጅግጅጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋል።

ሶስቱ መሪዎች የተገናኙት በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባሕር ቀጣና ውስጥ እየተካሄደ ያለው ዲፕሎማሲያዊ እና የደኅንነት አሰላለፍ ለውጥ በበረታበት ወቅት ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ፣ መሪዎቹ በጅግጅጋ የተገኙበትን ዓላማ ወይም አጀንዳ በተመለከተ የሰጠው ዝርዝር መረጃ የለም።

ይህ ጉብኝት የተከናወነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ ወደ ጅቡቲ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ጌሌ ጋር ውይይት ካደረጉና የዶራሌህ ወደብን ከጎበኙ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉበኝት ግብፅ ከጅቡቲ ጋር በወደብ ልማት፣ በሎጂስቲክስና በታዳሽ ኃይል ዘርፎች የትብብር ስምምነት መፈረሟን ተከትሎ የተደረገ እንደነበር ይታወሳል።

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ውይይቱ በጂኦፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች፣ በቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም የሁለትዮሽ ትብብርን በማጠናከር ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸው ነበር።

ዛሬ በጅግጅጋ የተደረገው ውይይት ሶማሊያ በዲፕሎማሲያዊና በደኅንነት ዘርፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገች ባለችበት ወቅት ነው። ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ቁልፍ ወዳጅ ከሆነችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር የነበራትን የደኅንነት ስምምነቶች በሙሉ ካቋረጠች በኋላ ከኳታር ጋር የመከላከያ ትብብር ስምምነት ተፈራርማለች።

በተጨማሪም ሳዑዲ ዓረቢያ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የቀጣናው ተፅዕኖ ላይ ገደብ ለመጣል ከሶማሊያና ከግብፅ ጋር ወታደራዊ ጥምረት ለመመሥረት በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ።

ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ በቀይ ባሕር ደኅንነትና በወታደራዊ ቅንጅት ላይ ያተኮረውን ይሄንኑ ስምምነት ለማፅናት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ግብፅ በሶማሊያ ያላትን ወታደራዊ ተሳትፎ እያስፋፋች መሆኑ የተዘገበ ሲሆን፣ የዚህም ዋነኛ ዓላማ ሶማሊላንድ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ለእስራኤል እና ለኢትዮጵያ ወታደራዊና ስልታዊ ጥምረት መሠረት ልትሆን ትችላለች የሚል ስጋት በመኖሩ የሶማሊያን መንግሥት ጥበቃ ቅድሚያ ለመስጠት እንደሆነ ተመልክቷል።

የጅቡቲ እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንቶች በጅግጅጋ መገኘት በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ እየታየ ያለውን ፈጣን የዲፕሎማሲ እና የደኅንነት አሰላለፍ ለውጥ በጉልህ የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህም የቀጣናው መሪዎች የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ትብብሮችን ለማጠናከር ጥረት እያደረጉ ባሉበት ወቅት የተከሰተ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...