Home ቢዝነስ ዜና ጣሊያን ለኢትዮጵያ የቡና ዘርፍ 10 ሚሊዮን ዩሮ ብድር አጸደቀች

ጣሊያን ለኢትዮጵያ የቡና ዘርፍ 10 ሚሊዮን ዩሮ ብድር አጸደቀች

ጣሊያን ለኢትዮጵያ የቡና ዘርፍ 10 ሚሊዮን ዩሮ ብድር አጸደቀች

የጣሊያን መንግስት የኢትዮጵያን የቡና ጥራትና ምርት ለማሳደግ 10 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ማፅደቁ ተነግሯል።

ብድሩ የኢትዮጵያን ቡና አምራቾች፣ አቅራቢዎችንና ሌሎች በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትን ይረዳል መባሉን ካፒታል ለመረጃው ለመረዳት ችሏል።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሪሚየም ጥራት ያለው ቡና ለማምረት እና የኤክስፖርት ገቢን ለማሳደግ የ15 ዓመት ስትራቴጂ እየተገበረች ቢሆንም በዘርፉ ካሉት ዋና ዋና ተግዳሮቶች መካከል አንዱ የፋይናንስ አቅርቦት ውስንነት እንደሆነ ተጠቁሟል ።

ኢትዮጵያ ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ በቡና የወጪ ንግድ 1.43 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን በዚህ በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 8 ወራት ውስጥ 157,000 ሜትሪክ ቶን ቡና በመላክ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ታዉቋል።CapitalNews