ፀደይ ባንክ እና ማስተር ካርድ አብረው ለመስራት ተስማሙ

Date:

ከተቋቋመ ሶስት አመትን በቀጣይ መስከረም 2018 የሚሞላው ባንኩ አለም አቀፍ ተቀባይነት ካለው ማስተር ካርድ ጋር የተዋዋለው ስምምነት እንዳስደሰተው ገልጿል።

በቀጣይ በ3 ዘርፎች ላይ ስምምነት እንዳደረገም የፀደይ ባንክ የዲጂታል ብራንች ባንኪንግ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ቴውድሮስ ታደሰ ተናግረዋል። ኢንተርናሽናል ካርድ፤ ካርድ አኳየር፤ ኮሚኒቲ ፓስ እንደሚሰኙም ገልፀዋል።

ፀደይ ባንክ ካለው ደንበኞች አንፃር ከባንኩ ጋር መስራት መቻላችን ትልቅ ስኬት ነው ሲሉ የማስተር ካርድ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ዳይሬክተር አቶ  እልፍ አገድ  በቀጣይ ባንኩን በሁሉም ረገድ ለመርዳት እንደሚሰሩም ገልፀዋል።

ባንኩ በሌላ በኩል ሰፖርት ኢዱኬሽን ከተሰኘ የትምህርት አስተዳደር ላይ ከሚሰራው ተቋም ጋር በጋራ የመስራት ስምምነት አከናውኗል።

የትምህርቱ ዘርፍ ላይ የሚስተዋለው ከወረቅት ጋር የተያያዘውን አሰራር ወደ ዲጂታላይዜሽን ለማዘዋወር አቅዶ ባለፋት አስር ዓመታት እየሰራ እንደሆነ የገለፁት የሰፖርት ኢዱኬሽንዋና ሥራ -አስፈፃሚ አቶ ሙልጌታ አሰፋ ናቸው።

ተቋሙ አሁን ላይ ከ 89 በላይ ትምህርት ቤቶች ጋር እየሰራም እንደሆነ ገልጿል።

ፕሮግራሙ ፀደይ ሰከላ እንደሚሰኝ የገለፁት የባንኩ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ቴውድሮስ ናቸው። በሞባይል ባንኪንግ ወይም በስድስት መቶ ሰላሳ የባንኩ ቅርንጫፍ መጠቀም እንደሚቻልም ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...