የሪፖርተር ጋዜጠኛ ታሰረ

Date:

የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አበበ ፍቅር ታሰረ፡፡ ጋዜጠኛ አበበ የታሰረው ትናንት ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት አካባቢ ነው፡፡

ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው ከልደታ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎች መረጃ በማሰባሰብ ላይ እያለ ሲሆን፣ የታሰረበት ምክንያት እስካሁን ግልጽ አልሆነም፡፡ ጋዜጠኛ አበበ በዕለቱ በፖሊሶች ተይዞ ከመወሰዱ በስተቀር በወቅቱ ወዴት እንደተወሰደና እንደታሰረ ባለመታወቁ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት በማድረግ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባደረገው ትብብር ጋዜጠኛው በልደታ ክፍል ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጌጃ ሰፈር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ ታውቋል፡፡

ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው እየሠራው ለነበረው ዘገባ ሚዛኑን ለመጠበቅ፣ የክፍለ ከተማውን ኃላፊዎች ለማነጋገር በሥፍራው በተገኘበት ወቅት ነበር፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጀግና በጦር ሜዳ ብቻ አይደለም የሚፈጠረው

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽነር ለሊሴ የካንሰር ሕመምን በጀግንነት እየተጋፈጡ ነው! የኦሮሚያ...

በተኪ ምርት ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማዳን ተቻለ

በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ሶስት ወራት በተኪ ምርት 1...

በዩኔስኮ ኢትዮጵያ 99 በመቶ ትመረጣለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ

በ43ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አጠቃላይ...

የሶሪያው ፕሬዚዳንት አሜሪካን የሚጎበኙ የመጀመሪያው የአገሪቱ መሪ ሊሆኑ ነው

የሶሪያ ፕሬዚዳንት አህመድ አል ሻራ በህዳር ወር መጀመሪያ ላይ...