ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዶናልድ ትራምፕ “ለጋዛ የሰላም ቦርድ አንድ ቢሊዮን ዶላር ከተያዘው የሩሲያ ሀብት ይውሰዱ” አሉ።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለጋዛ ኢኒሺዬቲቭ የቀድሞ የዴሞክራቶቹ አስተዳደር እንዳይንቀሳቀስ ካደረገው የሩሲያ ሀብት ገንዘብ እንዲወስዱ ሀሳብ ሰተዋል።
ለሩሲያ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፑቲን ሀሳቡን አቅርበዋል።
በጋዛ የሽግግር አስተዳደር ወቅት ለሚከወኑ ስራዎች ድጋፍ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እያሰባሰቡ ሲሆን ፑቲንም ለዐለም አቀፍ ሰላም አብረን እንቆማለን ብለዋል።
ፑቲን የትራምፕን የሰላም ቦርዱን ተቀላቀሉ ጥሪ በበጎ እመለከተዋለሁ ቢሉም ቦርዱን ለመቀላቀል ግን ስትራቴጂካዊ አጋሮቻችን ጋር መምከር አለብን የሚል ሀሳብ ሰተዋል።
ለመቀላቀል ከመወሰናችን በፊትም ቢሆን ትራምፕ 1 ቢሊዮን ዶላሩን ባይደን እንዳይንቀሳቀስ ካገዱት ሀብታችን ይውሰዱ የሚል ምክረ ሀሳብም አቅርበዋል።
ሞስኮ ከፍልስጤም ህዝብ ጋር የተለየ ግንኙነት እንዳላትም አስታውሰዋል ፑቲን።
ለግብዣው ትራምፕን ያመሰገኑት ፑቲን ጉዳዩን ለማጤን ግን ክሬሚሊን ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገዋል ብለዋል።
ፑቲን ከሩሲያ ሀብት ቀንሰው ትራምፕ ለሰላም ቦርዱ ይጠቀሙ ማለታቸው ምናልባትም ሌላ ፖለቲካዊ ግርግር በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘገባው የአር ቲ ነው።
