በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት በየዓመቱ በፈረንጆቹ ታኅሣሥ 10 ቀን የሚውለውንዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ በ2014 ዓ.ም. የተጀመረው ይህ ፌስቲቫል 5ኛ ዙር ትናንት መካሄዱን አራዳ ኤፍ ኤምሰምቷል።
የዘንድሮው ፌስቲቫልበኢሰመኮ የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት አሳሳቢ ተብለው በተለዩት በነጻነት መብት እና ትምህርት በማግኘትመብቶች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ጣቢያችን ከኮሚሽኑ ያገኘው መረጃ ያሳያል።
ዓመታዊው የሰብአዊመብቶች ፊልም ፌስቲቫል ዋነኛ ዓላማ ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች ቀን ለማሰብ፣ የኪነ-ጥበብን እና የሰብአዊ መብቶችን ትስስርለማጠናከር፣ ኪነ-ጥበብ “ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን ማየት የሚለውን የኢሰመኮ ራዕይ ለማሳካት እንዲሁምበሰብአዊ መብቶች ዙሪያ በተለያዩ ዘርፎች የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችንና ተቋማትን በአንድ ላይ በማሰባሰብ የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤንማስፋፋት እንደሆነም ተነግሯል።
