86ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ማንነትን፣ አብሮነትን እና ኢትዮጵያዊነትን በሚያጎላ መልኩ ይከበራል

Date:

በአድዋ ጦርነት ወቅት ፈረስ እና ፈረሰኞች ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይኾን ዘንድ በ1932 ዓ.ም በውስን ፈረሰኞች እንደተመሠረተ የሚነገርለት የአገው ፈረሰኞች ማኅበር በአሁኑ ወቅት ከ62 ሺህ በላይ አባላት ያሉት አንጋፋ ተቋም ስለመኾን ይነገራል።

ታሪክን ከባሕል ጋር አስተሳስሮ ዘመናትን የተሻገረው ማኅበሩ ዘንድሮ 86ኛ ዓመቱን ሊያከብር ዝግጅቱን አጠናቋል።

የበዓሉን አከባበር በተመለከተ ስለተደረጉ ዝግጅቶች መግለጫ ተሰጥተዋል።

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው ፈረስ በአገው ሕዝብ ዘንድ የክብሩ መጎናፀፊያ እና የአክብሮቱ መገለጫ መኾኑን ተናግረዋል።

86ኛው የአገው ፈረስ በዓል “የአብሮነት ቅርስ የሰላም ውርስ” በሚል መሪ መልዕክት ታሪኩን እና ባሕሉን በሚመጥን መልኩ በድምቀት ይከበራልም ነው ያሉት።

በበዓሉ ማንነት፣ አብሮነት እና ኢትዮጵያዊነት ከፍ ብለው ይታዩበታልም ብለዋል።

በድንቅ የፈረሶች ትርዒት ታጅቦ የሚከበረውን ይህን በዓል በመላው ኢትዮጵያ እና ከባሕር ማዶ ያሉ ወገኖች እንዲታደሙም ዋና አሥተዳደሪው ጥሪ አስተላልፈዋል።

የእንጅባራ ከተማ አሥተዳዳር ተቀደሚ ምክትል ከንቲባ የኔዓለም ዋሴ ይህ ታሪካዊ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከተማ አሥተዳደሩ ሁሉን አቀፍ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።

የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ ሃብት የኾነው ይህ በዓል የቱሪስት መስህብነቱን በሚያጎላ መልኩ እንደሚከበርም ተናግረዋል።

በበዓሉ የወጣቶች እና የሴቶች የፈረስ ላይ ትርዒቶችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፤ ለዚህም በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ሊቀ መንበር አልቃ ጥላዬ አየነው የአገው ፈረስ ባሕል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

86ኛው ዓመታዊ ክብረ በዓልም በዚህ የደስታ ስሜት ውስጥ ኾኖ በልዩ ድባብ ይከበራል ነው ያሉት።

86ኛው የአገው ፈረስ በዓል በመጪው ጥር 23/2018 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ በድምቀት ይከበራል።
(አማራ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...