ማስታወሻ

የኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ መልሕቅ – ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ

ግዮን መጽሔት :-የሚሊዮኖችን ህይወት ሲታደጉ የኖሩት ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ብዙ ማድረግ በሚችሉበት ዕድሜ እጅ ሰጡ፡፡ በህፃናት ቀዶ ጥገና በሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በሃገራችን ከሚገኙት ሁለት የህክምና ምሁራን ውስጥ አንዱ ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ነበሩ። ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ጥር 1 ቀን 1963 ዓም አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ። አባታቸው አቶ ታደሰ ሮበሌ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ (አሁን እማሆይ) እማሙ ገቢ ይባላሉ።  የመጀመሪያና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሃዋሳ ታቦር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሃዋሳ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁ ከመሆናቸውም በላይ በ1980 ዓ.ም የተሰጠውን ሃገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ወይንም ESCLC እጅግ ከፍ ያለ ነጥብ በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ  ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡ መንግስት በወቅቱ በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎችን በሚመድብበት የጎንደር ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተመድበው በ1981 የCommon Course ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋኩልቲ ካጠናቀቁ በኋላ ከ1982 ዓም ጀምሮ እስከ 1987 ድረስ ለስድስት ዓመታት የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው በማዕረግ ወይም በ Distinction በሐኪምነት ለመመረቅ በቅተዋል፡፡ ወደ ስራው አለም በመሰማራትም ከ1987 ዓም እስከ 1988 ዓም ድረስ በተመደቡበት የሆሳዕና ሆስፒታል በጠቅላላ ሐኪምነት፣ ከ1988 ዓም ጀምሮ ደግሞ ወደተማሩበት እና ወደተመረቁበት የጎንደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዝውውር በማድረግ በቀዶ ጥገና ክፍል ረዳት መምህርነት እና ጠቅላላ ሐኪም በመሆን ለሶስት አመታት ወገኖቻቸውን አገልግለዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰጠውን የሶስት ዓመታት የድህረ ምረቃ ትምህርት በመከታተል የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሐኪም ሆነው ከመመረቃቸውም በላይ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግም አግኝተዋል። በመቀጠልም ህንድ ሃገር በሚገኘው ቬሎር ክርስቲያን ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ የፌሎውሺፕ ትምህርታቸውን ተከታትለው በ1999 ዓም የህፃናት ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስት በመሆን ተመርቀዋል። ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከዚህ ሁሉ ትምህርት ጎን ለጎን በህክምናው ዘርፍም ከተመረቁበት ጊዜ አንስቶ እስከ 1988 ዓም ድረስ የሆሳዕና ከተማ እና የአካባቢውን ማህበረሰብ፣ ከዚያም እስከ ህዳር 2002 ዓም ድረስ ደግሞ የጎንደር ከተማና የአካባቢውን ማህበረሰብ፣ ከ2002 ዓም በኋላ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ ህሙማንን በተለይም ደግሞ ህፃናት ታካሚዎችን ከፈጣሪያቸው በተሰጣቸው ጥበብና ፀጋ አማካይነት ቀዶ ጥገና በማከናወን እንዲፈወሱ የሚያደርጉ ደከመኝን የማያውቁ ታታሪ የህክምና ባለሙያና ምሁር ነበሩ። በሌላ በኩል ደግሞ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለማስተማር የሚያስችላቸውን የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም Higher Diploma Program ተከታትለው ያጠናቀቁ ከመሆናቸውም በላይ በ2011 ዓም ደግሞ በጤና ባለሙያዎች ትምህርት Health Professional Education ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የቀዶ ጥገና ተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግም አግኝተዋል፡፡ ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ በርካታ ስልጠናዎችንና የአጭር ጊዜ ኮርሶችን የወሰዱ ሲሆን ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው። እንግሊዝ ሃገር በሚገኘው Paediatric Surgery at Leicester Royal Infirmary,...

በ103 አመታቸው ያረፉት የእማሆይ ዋሪት መልዕክት

ለምታከብሩኝና ለማከብራችሁ፤ ለምትመኩብኝና ለምመካባችሁ ለመርኬና አራዳ ልጆቼ እንዲሁም ወዳጆቼ! መልዕክቱ ሰፋ ያለና ረጅም ነበር፡፡ በሌላ ጊዜና በሌላ መድረክ እዘረዝረዋለሁ፡፡ ለዛሬው ግን በአጭሩ ወቅታዊውን ''እናታዊ መልዕክቴን'' ከመልዕክተኛዬ አድምጡት፡፡ ልጆቼ ሆይ!ትለፋላችሁ፤ ትደክማላችሁ፡፡ በእኩል ባይሆንም ታፈራላችሁ፤ ታገኛላችሁ! ግና ብዙዎቻችሁ...

ወንድሜን ለማታውቁት?!…

አያሌው ከበደ ተሰማ አስፍሽ የሁለት ታላቄ ነው፡፡ በመካከላችን ጠንሽ አለ፡፡ ብዙውን የልጅነትና የወጣትነት ጊዜያችንን አብረን ነው ያሳለፍነው፡፡ አንድ ቤት ውስጥ ተኝተን፣ አንድ ገበታ ከበን በልተን፣ አንድ ትምህርት ቤት ተምረን፣ ለአንድ እግር ኳስ ቡድን አንድ ማልያ...

ከብሔራዊ ቡድን ተጫዋችነት እስከ አመራርነት!

የአቶ አስፋው ከበደ የሕይወት ጉዞ! አቶ አስፋው ከበደ ከአባታቸው ከደጃዝማች ከበደ ተሰማ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ይታጠቁ ኪዳኔ በሕዳር 8 ቀን 1938 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ግንፍሌ እቃ ሰፈር በሚባል አካባቢ ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ...

ዶ/ር ጴሌ ዳሮታ …

(ፍልስፍናን ከነነፃነቷ የኖራት፣ በልዩ ትወና የሰበካት አይረሴ ምሁር!) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የነበረውን የጴሌ ዳሮታን (ዶ/ር) ህልፈት የሰማ ከቀድሞ ተማሪዎቹ የሆነ ‹‹አሳፍ ኃይሉ›› በማኅበራዊ ትስስር ገጹ፤ ስለ ጴሌ (ዶ/ር) ካሰፈረው ረዘም...

መጽሔቶች

ዜናዎች

spot_imgspot_img
በቅርብ የወጡ ጽሑፎች