የቤተ ክርስቲያኗ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ዓለም አቀፍ መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

Date:

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ 44ኛው ዓለም አቀፍ መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ አህጉረ ስብከት ተወካዮች እየተሳተፉ ሲሆን ፓትርያርኩ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን በጥበብ በመምራት፣ ለመጭው ትውልድ ማሻገር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡

በጉባኤው ላይ በቤተ ክርስቲያንና ገዳማት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች ቀርበው የመፍትሔ ሐሳቦች ይሰጥባቸዋል የተባለ ሲሆን፤ ቤተ ክርስቲያኗ ያከናወነቻቸው ተግባራት ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸውም ተጠቁሟል፡፡

በየዓመቱ በጥቅምት ወር በሚካሔደው በዚህ ጉባኤ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚጠቅሙ፣ ለመንፈሳዊ አስተዳደሯም የሚበጁ መሠረታዊ ጉዳዮች ይቀርባሉ። በሚቀርቡት ሪፖርቶች ላይም ውይይትና የልምድ ልውውጥ ተደርጎ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ይሸለማሉ፤ ዝቅተኛ አገልግሎት ይዘው የመጡ ደግሞ ከጉባኤው ልምድ ቀስመው አገልግሎታቸውን እንዲያሻሽሉ ይመከራሉ ተብሏል።

መደበኛ ስብሰባው ከዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በፖለቲካዊ ሳይሆን በቴክኒካዊ መንገድ መፈታት አለበት

በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ፣ እና የመካከለኛው ምስራቅ...

የ7 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ አለመከናወኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሚተዳደሩ 7 የጋራ መኖሪያ...

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ...