ስለ እኛ / About us

25 Years of Excellence in Print Media

Ethio Habesha Printing and Advertising PLC brings 25 years of expertise to the print media landscape. For over two decades, we have been the publishers of Ethio Habesha newspaper and Ghion magazine, two leading platforms that deliver insightful journalism. Throughout these years, we have consistently contributed original stories, in-depth articles, thought-provoking opinion pieces, and engaging essay series to inform and inspire our readers.

Our publications prioritize pressing social, economic, and political issues that significantly influence the country’s public discourse. By doing so, we strive to be a trusted voice on topics that matter most.

Our editorial approach emphasizes the importance of civic nationalism and multiculturalism, creating a harmonious platform that reflects the nation’s diversity while promoting unity.

At the heart of our success is a dedicated team of seasoned journalists, renowned for their expertise in breaking news, investigative reporting, and compelling feature writing—all conducted with strict adherence to journalism standards and ethics.

For more information and updates, visit us on YouTube and other platforms.

ከ25 ዓመታት በላይ የዳበረ የጋዜጠኝነት ልምድ

የግዮን መጽሔት ባልደረቦች በኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ውስጥ በጋዜጠኝነት ከ25 ዓመት በላይ የቆየን የሚዲያ ባለሙያዎች ነን። በኢትዮ ሐበሻ ኅትመትና ማስታወቂያ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ሥር የሚታተሙት “ግዮን” መጽሔት እና “ኢትዮ ሐበሻ” ጋዜጣ ስያሜያቸውን ሀገራዊ አድርገው በየሳምንቱ ለንባብ ይደርሳሉ።

መጽሔትና ጋዜጣችን በማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚ፣ በኪነጥበብ ጉዳዮች እንዲሁም በባሕል፣ ታሪክ እና ስፖርት ዙሪያ የሚያተኩሩ ሲሆን፤ “መለያችን ኢትዮጵያዊነታችን” በሚል መሪ ቃል እየተመሩ፤ በሀገሪቱ የነፃ ፕሬስ እንቅስቃሴ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሥራው ላይ በቆዩ ከፍተኛ ልምድን ያካበቱ ጋዜጠኞች በሚያቀርቧቸው መጣጥፎችና ጥልቅ ዘገባዎች፣ በታዋቂና አንጋፋ የቢዝነስ ሰዎች ጋር የሚቀርቡ ቃለ ምልልሶች፣ እንዲሁም ዕውቅና ያተረፉ ፀሐፊያን የሚሳትፉባቸው መጽሔት እና ጋዜጣ ናቸው።

“ግዮን” መጽሔት እና “ኢትዮ ሐበሻ” ጋዜጣ በሀገር ወስጥና በውጭ ሀገራት ካሉን ከፍተኛ ሥርጭት በተጨማሪ በዩቲዩብ፣ በቴሌግራም፣ በዌብሳይት፣ በX እንዲሁም በፌስቡክ ገጾቻችን ከፍተኛ ተከታይ ማፍራታችን ይታወቃል።

የግዮን መጽሔት ሥራዎችና የሥራ ሒደቶች

ዓላማ

  • በሀገራችን የተዳከመውን የንባብ ባሕል እንዲነቃቃ ማድረግና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ሐሳብ ማመንጨት የሚችል ዜጋ ማፍራት፣
  • ለኢትዮጵያ በርካታ ቁምነገሮች ያበረከቱ፤ ሆኖም ግን ሥራቸው የተዳፈነ ባለሙያዎችን መዘከርና ማስተዋወቅ፣
  • በዕድሜ፣ በዕውቀትና በሥራ ልምድ የካበተ ልምድ ያላቸውን አንጋፋ ሙያተኞች ከያሉበት አፈላልጎ በማናገር ሙሉ ልምዶቻቸውን እንዲያካፍሉና ካለፉት ያልተሣኩ ተሞክሮዎች ትምህርት እንዲገኝ የሚያስችሉ የመወያያ መድረኮችን መክፍት፣ ባሕሎችን፣ ትውፊቶችንና የአኗኗር ዘዬዎችን ይፋ በማድረግ ጠቀሜታቸውን ማጉላትና ሀገራዊ ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ መንቀሳቀስ፣
  • ኢትዮጵያዊ መሠረት የለውም የሚባለው የሀገራችንን የቴአትርና ፊልም ሂደት በባለሙያዎች እገዛ ሀገራዊ አቅጣጫ እንዲከተል የሚያስችል ጠቃሚና ገንቢ ሐሳቦችን ማስተናገድ (ማቅረብ)።

ራዕይ

በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት የተጠናከረ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አስፈላጊውን መሥዋዕትነት መክፈልና መጽሔታችን ኢትዮጵያዊ ይዘቷ በተጠበቀ ሁኔታ በምዕራቡ ዓለም “ምርጥ” የተሠኙ መጽሔቶች ከሚዘጋጁበት ደረጃ ላይ መድረስ።

ተልዕኮ

“ግዮን” መጽሔት የሣይንስና ቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑትን የተለያዩ የሕትመት ውጤቶችን በመጠቀም ጀማሪ የኾነውን የፕሬስ ነፃነት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርስ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ፤ እንዲሁም ዘመኑ የደረሰበትን የዲጂታል ቴክኖሎጂ በመጠቀም በልዩ ልዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሚዲያ መኾን።

አቋም

ከየትኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ገልተኛ በሆነ መልኩ ማኅበራዊና ጥበባዊ ዕሴቶቻችንን ላቅ ያለ ደረጃ እንዲደርሱ ማስቻል፣ የተከበሩ ሀገራዊ እሴቶቻችን ተጠብቀው እንዲቀጥሉ የበኩላችንን ሙያዊ ድርሻ መወጣት።