ሆፕ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ሰጠ

Date:

ሆፕ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር 2017 ዓ.ም በጀት አመት የ2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ የምክር ቤት ጉባዔ በዛሬው ዕለት አባላቱ በተገኙበት በኤልያና ሆቴል አካሄዷል።

ማህበር ከተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ1200 በላይ አባላትን ያፈራ ሲሆን ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ከ210 በላይ አባላቱን ተጠቃሚ ማረጉን ተገልጿል።

የማህበሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ አፀደ ፀሃዬ እንደተናገሩት ማህበራቸው ከተመሰረተ ሁለት አመት ከሰባት ወሩ ቢሆንም ነገር ግን እጅግ ከፍተኛ ካፒታል እና ብዙ አባላት ያፈራበት ዘመን ነው። በዚህ ከቀጠለ ደግሞ ከዚህ በላይ ስኬታማ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

የዛሬው ጉባዔ ዋናው አላማው የማህበሩ አባላት ምክር ቤት ተቋሙ ምን ላይ እንደደረሰ እቅዱን ሪፖርቱን አውቀው ለቀጣይ በጀት አመት አጋዥ ሁነው ተጠቃሚነቱን ለማስፋት ለአባላት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነቱን ለማስፋት እንደሆነ ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።

ሆፕ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር የተቋቋመው በአተዮጵያ የህ/ስ/ማ አዋጅ መሰረት በቁጥር 985/2009 ሲሆን ህጋዊ ስብእናው ከየህ/ስ/ማ ማደራጃ ቢሮ ፍቃድ አግኝቶ በስራ ላይ ይገኛል።ሆፕ በቀዳሚነት የሚያንቀሳቅሰው የአባላት መደበኛ ቁጠባና አክስዮን በመሰብሰብ የተሻለ የብድር አገልግሎት በማቅረብ የተሳለጠ የማህበራዊ ግንኙነቶች እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች በአባላትና በማህበሩ እንዲኖር ማድረግ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሙፍቲ ቀደምት ፎቶግራፍ

ይህ ፎቶግራፍ የተነሳው በ1965/1966 ሲሆን በፎቶው የሚታዩት የኢትዮጵያ እስልምና...

አገር ጥቁር ትልበስ!

ቃለ መጠይቅ የማድረግ እድል ሳገኝ ኢቲቪ ገብቼ ዓመትም አልሆነኝ።...

ታላቅ አረጋዊ ፣ የበሳል አእምሮ ባለቤት፣ አገርን የሚወዱ…

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት...

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ሽኝት እየተደረገለት ነው

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ከመኖሪያ ቤታቸው...