ለአራት ሙዚየሞች የብቃት ማረጋገጫ እውቅና ተሰጠ

Date:

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለሚገኙ አራት ሙዚየሞች የብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና ሰጠ፡፡

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት በተካሄደ መርሀ ግብር እውቅናው የተሰጣቸው በኦሮሞ ባህል ማዕከል የኦሮሞ ሙዚየም፣ የወለጋ ሙዚየም ፣ የጅማ ሙዚየምና የመልካ ቁንጥሬ ባልጭት መካነ ቅርስ ሙዚየም ናቸው፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ደራራ ከተማ ባደረጉት ንግግር ለሙዚሞቹ የተሰጠው የብቃት ማረጋገጫ የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጠ።

ለሙዚየሞቹ ተጨማሪ አቅም ከመስጠቱ ባሻገር ህጋዊነታቸው እንዲጨምርና የበለጠ ለመስራትና ቅርሶቹን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ የሆነ እድል እንደሚፈጥርላቸው ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የሙዚየም ኢግዚቢሽን ዝግጅት ዲስክ ኃላፊ አቶ በረከት ዘውዴ በበኩላቸው የሙዚየም የሙያና የብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና አሰጣጥ በሀገሪቱ የሚገኙ ሙዚየሞች ባላቸው የቅርስ ስብስብ ዓይነት፣ በቅርስ አያያዝና አጠባበቅ፣ በጥናትና ምርምር፣ በቅርስ ስብስብ ስነዳና ጥበቃ፣ በሰው ኃይልና በመዋቅራዊ አደረጃጀት፣ በዐውደ ርዕይ ዝግጅትና የትምህርት አገልግሎት ጥራትና ደረጃ ተለይተው የሚጠበቅባቸውን መመዘኛ መስፈርቶችን በማሟላት ለጎብኝዎቻቸውና ለተመራማሪዎች ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እንደሚጠቅም አብራርተዋል ፡፡

በባለስልጣኑ የሙዚየም ትምህርት ዲስክ ኃላፊ አቶ ንጉሱ መኮንንን ዓባይ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የብቃት ማረጋገጫ እውቅናው በሀገሪቱ ሙዚየሞች መካከል ሊኖር የሚገባው ህጋዊና ተመጋጋቢ የሥራ ግንኙነት ግልፅ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ፣ ሙዚየሞችም ብቁና ተወዳዳሪ ይሆናሉ።

ለሀገሪቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ የሚያበረክቱበትን አቅም ለመፍጠር እንደሚያስችል ጠቁመው ሙዚየሞቹ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲያገኙ ፣ አገልግሎታቸውን እንዲያሻሸሉ ፣በሚሰጣቸው የሙያና የብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና የምስክር ወረቀት መሰረት ልዩ ልዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ፣ ለሙዚየሞቹ ብቃት መሻሻል የክትትልና ድጋፍ አመቺ መደላደል ለመፍጠር እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡

ባለስልጣኑ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ሙዚየሞች ዛሬ የተሰጠውን ጨምሮ መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ አስራ ሁለት ሙዚየሞች እውቅና ሰጥቷል፡፡

በክልል ደረጃ በአንድ ቦታና ቀን ለአራት ሙዚየሞች የብቃት ማረጋገጫ እውቅና ሲሰጥ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቀዳሚ ሆኗል ፡፡
(ቅርስ ባለስልጣን)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢትዮጵያ የ1 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ዕዳዋን ለማዋቀር ስታደርግ የነበረዉ ድርድር ያለ ስምምነት ተቋረጠ

የኢትዮጵያ መንግሥት በ2024 ዓ.ም. ዋናው ዕዳ የሚከፈልበት የአንድ ቢሊዮን...

የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፍ ዛሬም በሌላ አቅጣጫ ቀጥለዋል

በመቐለና ዙሪያዋ የሚገኙ የትግራይ ኃይል አባላይ ትናንት ሰኞ ጥቅምት...

የምርመራ ኬዝ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል

ተማሪ ሊዛ ደሳለ የተባለች ወጣት ሰሞኑን በደሴ ከተማ “...

ስቲሊ አር.ኤም.አይ ላለፉት አራት ዓመታት የፕላቲኒየም ሸልማት ተሸላሚው

የ2017 በጀት ዓመት 7ኛው የታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅና እና...