ለአሽከርካዎች ቅሬታ ምላሽ 

Date:

በአገራችንም ሆነ በከተማችን ለትራፊክ አደጋ መከሰት ብሎም ለዜጎች ሞት ለአካል መጉደል እና ለንብረት መውደም ምክንያቶ ተብለው በጥናት ከተለዩት 5 ዋና ዋና ጉዳዮች ውስጥ በአሽከርካሪዎች የሚደረግ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ግንባር ቀደሙ ነው፡፡

ይሄንኑ ለከግምት ውስጥ በማስገባት የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ በተለያዩ አከባቢዎች  በፍጥነት ምክንያት የትራፊክ አደጋ የሚደርስባቸውን ቦታዎች (Black spots) በመለየት የፍጥነት ማብረጃ እና መገደቢያ ጉብታዎችን(Speed Humps) ይሰራል፡፡

ሰሞኑን ከሃጫሉ አደባባይ እስከ ሃይሌ ጋርመንት በሁለቱም አቅጣጫዎች እና ከሃይሌ ጋርመንት ሃና ማሪያም መስመሮች ላይ በተገነቡ የፍጥነት ማብረጃዎች አከባቢ ለአሽርካሪዎች ጉብታ መኖሩን የሚያመላክቱ ከወትሮው ለየት ያለች 25 መረጃ ሰጪ የጉብታ ምስል ያላት ምልክት ባለስልጣን መ/ቤቱ መትከሉ ይታወሳል፡፡

ነገር ግን ባለፉት ሁለት ቀናት ከሃጫሉ አደባባይ እስከ ሃይሌ ጋርመንት ባለው መንገድ ላይ በተተከሉ ጉብታዎች ዙሪያ ከተለያዩ መንገድ ተጠቃሚ ማህበረሰብ በተለይም ከአሽከርካሪው አከባቢ ምልክቶች እንዴትና የት እንዲሁም አለም አቀፍ ከፍታ እና አቀማመጥ በተከተለ መልኩ ነው ሊተከሉ የሚገባው የሚል ቅረታ በተደጋጋሚ ይቀርብ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ ልብ ብሎ ላየው በአከባቢው መንገድ ላይ ባሉ ጉብታዎች ጋር  አሽከርካሪው ከመድረሹ 50 ሜትር ቀደም ብሎ አለም አቀፍ ስታንዳርዱን የጠበቀ የጉብታ ማመላከቻ ተተክሏል፡፡ ሰሙንኑ አጠር ያሉ ጉብታ ያሉ ጉብታ ማመላከቻዎች የተተከሉት በምሽት የአሽከርካሪዎን እይታ ለመጨመር ጉባታው ባለበት የተተከሉ መሆናቸውን ማስተዋል እና መረዳት ይገባል ሲል ባለስልጣን መስሪያቤቱ ያስገነዝባል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የስደትና መፈናቀል ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል

በተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ፕሬዚዳንት አልሲሲ ፊት ለፊት ሊገናኙ?

አብይ አህመድ እና አበዱልፈታህ አልሲሲ ፊትለፊት እንዲገናኙ እንደምትፈልግ አሜሪካ...

በትግራይ ጦርነትን ከማስቀረት ሰሞኑን እየተካሄዱ ያሉት ሰልፎች መበረታት አለባቸው

ላለፉት ተከታታይ ቀናት በርካታ ጥያቄዎችን ያነገቡ የቀድሞ ተዋጊዎች በትግራይ...

ግብፅ እና ሱዳን በዓባይ ውኃ እና በሱዳን ቀውስ ዙሪያ ተወያዩ

የግብፁ ፕሬዝደንት ዐብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር...