ለኢትዮጵያ የ110 ሚ. ዶላር ድጋፍ ቃል ተገባ

Date:

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ ለገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም የሚውል የ110 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል፡፡

ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን፣ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽንና ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ አቶ አህመድ ሺዴ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት እና በሴቶች የስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

በቀጣይም ባንኩ በገጠር አካታች እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት (RISED) ኢኒሼቲቮች እንዲሁን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የዓለም አቀፍ አጋርነት ዳይሬክተር ቱራያ ትሪኪንቱራያ ትሪኪን በበኩላቸው÷ ተቋማቸው ለገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም (RUFIP III) ሶስተኛ ምዕራፍ ማስፈጸሚያ የሚውል የ110 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደረግ ገልፀዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ። ዛሬ ሰባት...

ለዩክሬን ሰላም ‘በጣም ተቃርበናል’ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በትናንትናው...

በዲማ የአለባበስ ቅጣት

በጋምቤላ ክልል ዲማ ከተማ ከባህል ውጪ በሆነ አለባበስ ምሽት...