ለዩክሬን ሰላም ‘በጣም ተቃርበናል’ ትራምፕ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በትናንትናው ዕለት በዋይት ኅውስ  ውይይት አድርገዋል። ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በቅርቡ ያደረጉትን የስልክ ውይይት፣ የዩክሬን ግጭት መፍትሄ አቅጣጫ እና በቅርቡ በቡዳፔስት የታቀደውን ድርድር ውይይት ተካሂዶበታል።

👉 ትራምፕ በስብሰባው ወቅት ሰላም የማምጣት ተስፋ እንዳላቸው የገለፁ ሲሆን የሰላም ሂደቱ ጥሩ ደረጃ ላይ እና ወደ ፍጻሜው ላይ እየደረሰ መሆኑን አስታውቀዋል። እንዲሁም ከኪዬቭ እና ከሞስኮ ጋር ለሚያደርጉት ድርድር ያቀዱትን ስትራቴጂ አስቀምጠዋል።

ከትራምፕ ንግግር የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች

⚫️ ስለ ሰላም ድርድር፡ “በዩክሬን ሰላም ላይ ታላቅ መሻሻል እያሳየን ነው፤ እናሳካዋለን ብዬ አስባለሁ።”

⚫️ ከፑቲን ጋር ስላደረጉት ውይይት፡ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ጋር በቅርቡ በስልክ ያደረጉትን ውይይት ዝርዝር መረጃ ከዘለንስኪ ጋር በሚያደርጉት ውይይት ወቅት እንደሚያጋሩ ጠቁመዋል።

⚫️ ስለ ቡዳፔስት መመረጥ፡ ከፑቲን ጋር ለሚያደርጉት ስብሰባ ቡዳፔስት ለምን እንደተመረጠች ለተጠየቁት ጥያቄ  “ምክንያቱም ኦርባንን ስለምንወደው ነው” ብለዋል።

⚫️ ስለ ስብሰባው ቅርፅ፡ ከፑቲን እና ከዘለንስኪ ጋር ሊደረግ ስለሚችለው  የሦስትዮሽ ጉባኤን አስመልክቶ “መካሄዱ አይቀርም፣ ሁለት ስብሰባ ይሆናል” ብለዋል።

⚫️ የፑቲንን አቋም አስመልክቶ፡ “ፑቲን የዩክሬንን ግጭት መቋጨት የሚፈልግ ይመስለኛል።”

⚫️ ግጭት ማባባስን ስለ ማስወገድ፡ “ግጭቱን ስለ ቶማሃውክ ሳናስብ ማቆም እንችላለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ቶማሃውኮች ትልቅ ነገር ናቸው እና ግጭቱን እንዲባባስ ሊያደርጉ ይችላሉ።”

⚫️ ግዛትን መልሶ ስለ ማግኘት፡ ዩክሬን ያጣቻቸውን ግዛቶችን መልሳ ስለማግኘት ለተጠየቁት ጥያቄ ትራምፕ፣ “መቼም አታውቁም” ብለዋል።

⚫️ ስለ ሰላም ቅድመ ሁኔታዎች፡ “መፍትሄ እንዲመጣ ፑቲን እና ዘለንስኪ ትንሽ መግባባት አለባቸው።”

⚫️ ስለ ቻይና ሚና፡ ትራምፕ ከቤጂንግ ጋር በዩክሬን ጉዳይ ላይ እየተነጋገሩ መሆኑን ጠቅሰው፣ “ግጭቱ በፍጥነት እንዲያልቅ እፈልጋለሁ” ብለዋል።

⚫️ የድሮን ትብብርን በተመለከተ፡ አሜሪካ ከዩክሬን ጋር የድሮን ቴክኖሎጂ ልውውጥን እየፈለገች ነው፤ “በጣም ጥሩ ድሮን ይሰራሉ” በማለት ትራምፕ አስተያየት ሰጥተዋል። ብዛት ያለው የሚሳኤል ክምችት የመያዝ አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበዋል።

⚫️ የሩሲያ-አላስካ ማስተላለፊያ መስመር፡ ሩሲያን እና አላስካን ሊያገናኝ ስለሚችለው በዕቅድ ላይ ያለ መሿለኪያን በተመለከተ ለተጠየቁት ጥያቄ ትራምፕ “ጥሩ ነገር” ሲሉ ገልጸው፣ “ላስብበት ይገባል” ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ። ዛሬ ሰባት...

በዲማ የአለባበስ ቅጣት

በጋምቤላ ክልል ዲማ ከተማ ከባህል ውጪ በሆነ አለባበስ ምሽት...

ለኢትዮጵያ የ110 ሚ. ዶላር ድጋፍ ቃል ተገባ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ ለገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም...