የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ ጦርነቱን የማታቆም ከሆነ የቶምሀውክ ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ለዩክሬን እልካለሁ አሉ፡፡
ትራምፕ ይህንን ያሉት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ በስልክ ካወሩ በኋላ ነው ተብሏል፡፡
ቮለድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ እያደረሰችብን ላለው ጥቃት ምላሹን ልንሰጥ ይገባል በዚህም ሚሳኤሉ በእጅጉ ያስፈልገናል ማለታቸውም ተገልጿል፡፡
ሞስኮ ዋሺንተን ሚሳኤል ለኬቭ የምትልክ ከሆነ ጦርነቱን ታፋፍመዋለች፤ ከአሜሪካ ጋርም ቢሆን መቃቃር ውስጥ እንገባለን ብላለች፡፡
ቶም ሀውክ ሚሳኤል 2ሺ 500 ኪሎ ሜትር ወይንም 1ሺ 500 ማይል የመምዘግዘግ አቅም አለው፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ወደ እስራኤል በሚያቀኑበት ወቅት ነው፤ ከሪፖርተሮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ቶምሀውክ ሚሳኤል ለዩክሬን የመላክ እድል ይኖራል ያሉት፡፡
በቶምሀውክ ሚሳኤል በሚልኩበት ሁኔታዎች ዙሪያ ከሩሲያ ጋር ንግግር እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነዉ