ከባንኮች ከፍተኛ ድርሻ የሚገዙ አካላት የገንዘባቸውን
ምንጭ እንዲያሳውቁ የሚያስገድድ ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ
ብሄራዊ ባንክ፣ የባንኮችን ከፍ ያለ መጠን ያላቸው የአክሲዮን ዝውውሮች ለመቆጣጠር ወይም ለማገድ ሥልጣን የሚሠጠውን ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
ረቂቅ መመሪያው፣ ከባንኮች ከፍተኛ ድርሻ የሚገዙ አካላት የገንዘባቸውን ምንጭ እንዲያሳውቁ የሚያስገድድ ነው።
መመሪያው፣ የአክሲዮን ዝውውሮች ግልጽና ዓለማቀፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ እንዲካሄዱ ለማረጋገጥ ያስችላል ተብሏል።
ባንኩ ረቂቅ መመሪያውን ለባለድርሻ አካላት ውይይት ማቅረቡን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ገልጧል።
ዋዜማ-