አንዳንድ ጥናቶች ከስክሪን የሚመነጨው ሰማያዊ ጨረር የእንቅልፍ ጊዜ መድረሱን ሰውነታችን እንዲረዳ የሚያደርገውን ሜላቶኒን የሚባለውን ሆርሞን ስለሚቀንስ እንቅልፍን አስቸጋሪ እንደሚያደርግ አሳይተው ነበር።
ግን ከዚህም የባሰ አደጋ እንዳለው ነው የተገለጸው።
የኦክስፎርድ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አንድሪው ፕዝቢልስኪም ሆነ ፕሮፌሰር ኤቸልስ፤ ለልቅ እና ጎጂ ይዘቶች እንደመጋለጥ ያሉ የኦንላይን ልምምዶች የሚደቅኑትን ከባድ ጉዳይ አይክዱም።
ነገር ግን ሁለቱም በስክሪን ጊዜ ዙሪያ ያለው ክርክር ተጠቃሚዎች ልምዳቸውን እንዲደብቁት ሊያደርጋቸው ይችላል የሚል ስጋትን ያነሳሉ።
አሁን ላይ፤ ልጆችን ከስክሪን መለየት ጥርጣሬ የሚያሻው ጉዳይ አይደለም ብላ ታምናለች።
ወላጆች በተቻለ መጠን ልጆቻቸውን ከስማርት ስልክ እንዲለዩ ትወተውታለች።
የወጣቶች የስክሪን አጠቃቀምን በተመለከተ በሚደረጉ ጥናቶች ላይ የሚሰበሰበው መረጃ በአብዛኛው በራስ ሪፖርት የተደረገ መሆኑን ብትስማማበትም፤ ይህ ብቻውን ማስረጃውን ውድቅ አያደርገውም ትላለች።
89 ቤተሰቦች 181 ልጆችን ያካተተ አንድ የዴንማርክ ጥናት በ2024 ታትሞ ነበር።
ከጥናቱ ተሳታፊዎች ግማሾቹ፤ ለሁለት ሳምንት የስክሪን ጊዜያቸው በሳምንት ለሦስት ሰዓታት ብቻ እንዲሆን ተገድቦ፤ ታብሌቶቻቸውን እና ስማርት ስልኮቻቸውን አስረክበዋል።
የጥናቱ ውጤት፤ የስክሪን ጊዜን መቀነስ “በሕፃናት እና በጉርምስና ዕድሜ ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር” እና “ማኅበራዊ ባህርይን” እንደሚያጠነክር ደምድሟል።
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ምርምር እንደሚያስፈልግም ግን ጠቁሟል።
ብዙውን ጊዜ ከመጥፎ ዜና ጋር ተያይዞ የሚነሳው ረጅም ጊዜ ስክሪን ላይ መቆየት፤ በድብርት የሚጠቁ ወጣቶች ቁጥር ለመጨመሩ፣ ከባህርይ ጋር ለተያያዙ ችግሮች እና የእንቅልፍ እጦት መከሰት ተጠያቂ ተደርጎ ይጠቀሳል።
ታዋቂዋ የኒውሮሳይንስ ተመራማሪ ባሮኔስ ሱዛን ግሪንፊልድ ደግሞ፤ ኢንተርኔትን መጠቀም እና የኮምፒውተር ጨዋታዎች (games) በአስራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆች አንጎልን ይጎዳል እስከ ማለት ትደርሳለች።
በአውሮፓውያኑ 2013 ባደረገችው ጥናት ረጅም የስክሪን ጊዜን የሚያስከትለው ጉዳትን ስለ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ሲነሳ ከነበረባቸው የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ጋር አነጻጽራለች።
በብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል ላይ የወጣ አንድ ርዕሰ አንቀጽ፤ ባሮኔስ ግሪንፊልድ ስለ አንጎል ያቀረበችው ሀሳብ “በሳይንሳዊ ማስረጃዎች ላይ የተመሠረተ አይደለም… እንዲሁም ለወላጆችም ሆነ ለጠቅላላው ሕዝብ አሳሳች ነው” በማለት ተከራክሯል።
አሁን ደግሞ ሌላ የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ቡድን፤ ረጅም የስክሪን ጊዜ ጉዳቶችን በተመለከተ ተጨባጭ ሳይንሳዊ ማስረጃ ይጎድላል ብሏል።
BBC