የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ሽልማትን ለሜቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር መታወሻነት እንዲሆንለት ሰይፉ ፋንታሁን ጠይቋል፡፡
በሚዲያው ዘርፍ የዘንድሮ የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚ የሆነው ታዋቂው የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያው ሰይፉ ፋንታሁን ይህ ሽልማት ሜቄዶንያን ለማስታወስ ሊሆን እንደሚገባ አስታውቋል፡፡
በዘንድሮ የ2025 የአፍሪካ ኢምፓካት አዋርድ የአየር መንገዱ አቶ መስፍን ጣሰው፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ፣ ጆ ማሞ እና ሰይፉ ፋንታሁንን ተሸላሚ አድርጓል፡፡
ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ስነ ስርአት በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የሚሰናዳ ነው።
በየአመቱ ከስፖርት፣ ከስነ ጥበብና ከስራ ፈጠራ ዘርፎች ለማህበረሰቦቻቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦና ለለውጥ ላደረጉት የላቀ ተሳትፎ ከየዘርፉ ተመርጠው የሚሸለሙበትም መድረክ ነው።