ዳሸን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ግለሰብ ደንበኞች፣ ነጋዴዎች እንዲሁም ወኪሎች በቴሌብር የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት እንዲያገኙ ባቀረበው አገልግሎት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 14 በሊዮን ብር ብድር መማቅረቡን አስታውቋል፡፡
መደበኛ የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ላልሆነው የማህበረሰብ ክፍል መሻሻል ከፍተኛ ሚና ያላቸውን፣ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ የሞባይል አነስተኛ ብድር፣ የኦቨር ድራፍትና የቁጠባ አገልግሎቶች ዳሸን ባንክ በዚህ አገልግሎት እያቀረበ ነው፡፡
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ2.3 ሚሊዮን በላይ የሚደርሱ ደንበኞች በቴሌብር አማካኝነት ከዳሸን ባንክ ከ8.4 ሚሊዮን በላይ መጠን ያላቸው የገንዘብ ዝውውሮችን (ትራንዛክሽኖችን) ፈፅመው 14 ቢሊዮን የሚደርስ ብድር እንደቀረበላቸው ባንኩ ያስታወቀው።
ዳሸን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በአጋርነት የግለሰብ ደንበኞች፣ ነጋዴዎች እንዲሁም ወኪሎች “መላ” የተሰኘውን የአነስተኛ ብድር አገልግሎት፣ በቴሌብር በአካውንታቸው ላይ ያላቸው ቀሪ የሂሳብ መጠን በቂ ባልሆነበት ጊዜ የሚጠቀሙት “እንደኪሴ” የተሰኘ የክሬዲት ክፍያ(ኦቨርድራፍት) ብድር አገልግሎት እያቀረበ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም “ሳንዱቅ” የተሰኘ ደንበኞች ከወለድ ነጻ ወይም የተለያየ የወለድ መጠን የሚታሰብባቸው የቁጠባ አይነቶች በዚህ አገልግሎት መቅረቡን ባንኩ አስታውቋል፡፡