በ2017 በጀት ዓመት 4 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በተኪ ምርት የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን የጠቆመው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ በተያዘው በጀት ዓመት ደግሞ 5 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት መታቀዱን አስታውቋል።
ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደተናገሩት ባለፉት ሦስት ወራት ወደ ውጭ ከተላከ ምርት ከ98 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱንና ይህ ውጤት በ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ችግሮችን በመፍታት ምርታማነትን በማሳደግና ባለሃብቶችን በመሳብ እንደተገኘ ገልጸዋል።