በእስራኤል የተከሰተውን ሰደድ እሳት በመቆጣጠር መንገዶች ተከፈቱ

Date:

የእስራኤል የእሳት አደጋ ተከላካዮች ቡድን በእየሩሳሌም አቅራቢያ የሚደርሰውን ሰደድ እሳት ለሁለተኛ ቀን ለማጥፋት ሲታገሉ የቆዩ ሲሆን፥ የተዘጉ በርካታ ዋና ዋና መንገዶችም መከፈታቸውን ፖሊስ አስታውቋል። እሳቱ እሮብ እለት የተቀሰቀሰው በዋናው እየሩሳሌም ከቴል አቪቭ በሚያገናኘው አውራ ጎዳና ላይ ሲሆን ፖሊሶች መንገዶቹን በመዝጋት በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን በአቅራቢያው ካሉ አካባቢዎች እንዲወጡ አድርገዋል።

የእስራኤሉ የእሳት አደጋ መከላከያ አገልግሎት 163 የምድር ሰራተኞች እና 12 አውሮፕላኖች እሳቱን ለመቆጣጠር እየሰሩ ነው ብሏል። የነፍስ አድን ኤጀንሲ ኃላፊ ማጌን ዴቪድ አዶም ረቡዕ እለት ብቻ 23 ሰዎች ህክምና ድጋፍ እንዲያገኙ መደረጉን ገልፀዋል። የእስራኤል የህዝብ መገናኛ ብዙሃን ካን እንደዘገበው 17 የእሳት አደጋ ተከላካዮችም ቆስለዋል ብሏል። የእሩሳሌም-ቴል አቪቭ መንገድን ጨምሮ ዋና ዋና መንገዶች እንዲከፈቱ በማድረግ ሰራተኞች ሌሊቱን ሙሉ ሰርተዋል ሲል ፖሊስ አስታውቋል።”ሁሉም መንገዶች ለትራፊክ ክፍት ሆነዋል” ሲል የፖሊስ መግለጫ ይፋ አድርጓል። በከፍተኛ ሙቀት እና በጠንካራ ንፋስ የተደገፈው እሳቱ በደን የተሸፈኑ አካባቢዎች በፍጥነት በመዛመታቸው ከአምስት ያላነሱ ማህበረሰቦች ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ፖሊስ ገልጿል።የአውሮፓ ሀገራት ኢጣሊያ እና ቆጵሮስ የአደጋ ጊዜ ጥረቱን ለመደገፍ ስምንት የእሳት አደጋ መከላከያ አውሮፕላኖችን ልከዋል ሲል የእስራኤሉ ዘ ታይምስ ዘግቧል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እሳቱ ወደ እየሩሳሌም ሊዛመት እንደሚችል በማስጠንቀቅ “ብሔራዊ ድንገተኛ” አዋክ አውጀው ነበር። የእስራኤል ጦር ሰራተኞች እየሩሳሌም እና ሌሎች ማእከላዊ ወረዳዎች እየረዱ መሆናቸውን ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቃል አቀባይዋ ዩክሬን የአፍሪካ ሀገራትን መበቀል ትፈልጋለች አሉ

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ ኪዬቭ የአፍሪካ አገራት...

ሕጻኑ በሀገሪቱ የመጀመሪያ በሆነ ቀዶ ሕክምና ተወለደ

የ28 ዓመቷ ወይዘሮ ሰናይት ታምራት ቀደም ሲል በነበረው እርግዝናዋ...

ግብፅ የኤርትራን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብድል ፈታህ አልሲሲ፤ የኤርትራን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት...