በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው

Date:

68 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጀልባ መስጠም አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።

በየመን አብያን ግዛት ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በመስጠሟ ቢያንስ 68 ስደተኞች መሞታቸውንና 74 ስደተኞች ደግሞ የደረሱበት እንደማይታወቅ ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።

በየመን የድርጅቱ ተወካይ አቤዱሳቶር ኢሶቭ ለአሶሼትድ ፕሬስ በሰጡት ቃል ” በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ #ኢትዮጵያውያን ናቸው ” ብለዋል።

ኢሶቭ በሰጡት ቃል፤ ‘ ካንፋር ‘ በተባለ አካባቢ የ54 ስደተኞች አስክሬን በውቅያኖስ ዳር የተለያየ ቦታ ወድቆ መገኘቱን በሌላ ቦታ የተገኘ 14 አስክሬን ወደሆስፒታል መላኩን ተናግረዋል።

12 ሰዎች ደግሞ በህይወት መትረፋቸው ተመላክቷል።

እንደ ተወካዩ ገለፃ ኢትዮጵያውያኑ አደጋው የደረሰባቸው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው።

@tikvahethiopia @thiqahEth

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢመማ 23ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተሞች ተካሔደ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻው ሥነ_ሥርዓት...

ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ...