ቨርቹዋል እስተዲ አርቲስት ሰሎሜ አዳምን የድርጀቱ ብራንድ አምባሰደር አድርጎ መረጠ። ድርጅቱ ላለፉት 3 ዓመታት ከ 4ኛ እስከ 12ኛ ያሉ ተማሪዎችን ብቃት ባላቸው መምህራን፤ በበይነ መረብ ሲያስጠና መቆየቱን ገልጿል።
ተማሪዎች ባሉበት ሆነው ቋንቋ እና የተለያዩ አጫጭር ሥልጠናዎችን እየተከታተሉ ነው ያለው ድርጅቱ፤ በቀላሉ ለመማር የሚረዱ መንገዶችን በመጠቀም እያስተማረ እንደሆነ አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም ለክልልና የሀገር ዓቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ልዩ ድጋፍና እገዛ እንደሚያደርግ የገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይም የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማጠናከር ብራንድ አምባሳደር መምረጡን ጠቁሟል።