በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ፉልሃምን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ከባድ ፉክክር በተደረገበት ጨዋታ አርሰናል ፉልሃምን በሜዳው እና ደጋፊው ሲያሸንፍ÷ የማሸነፊያ ግቡን ሊዮናርዶ ትሮሳርድ አስቆጥሯል።
ቀደም ሲል በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 0፣ ማንቼስተር ሲቲ ኤቨርተንን 2 ለ 0፣ ብራይተን ኒውካስልን 2 ለ 1፣ በርንሌይ ሊድስ ዩናይትድን 2 ለ 0፣ ሰንደርላንድ ወልቭስን 2 ለ 0፣ ክርስታል ፓላስ እና በርንማውዝ 3 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።