“አሰብ ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ነው! የትኛውንም ዋጋ ከፍለን እናስመልሰዋለን” ሲሉ ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ ገለፁ።
“አሰብ የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ግዛት ነው የኢትዮጵያም ህልውና ነው፤ በኢትዮጵያ ጉዳይ የመወሰን መብት ባልነበረው የሽግግር ቡድን አሳልፎ የተሰጠ ራስ ገዝ የባህር በራችን ነው፤ በዚህም ብዙ ሃገራት በናንተ ድክመት ነው እስካሁን ያልተመለሰው እንጂ እስካሁን መቆየት ያልነበረበት ነው ይሉናል ፤ አሁን ላይ የቀይ ባህር ጉዳይ የህልውናችን ጉዳይ ሆኗል ለህልውናችን ስንልም የትኛውን ዋጋ ከፍለን አሰብን እናስመልሰዋለን ።”
ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ ይህንን ያሉት በፕራይም ሚዲያ በነበራቸው ቆይታ ነው፡፡