አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የዓለም አቀፉ የልማት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

Date:

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከእንግሊዝ የአለም አቀፍ የልማት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ባሮነስ ጄኒ ቻፕማን ጋር በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ካለው የዓለም ባንክ እና የአይኤምኤፍ ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በእንግሊዝ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የቆየ አጋርነት በማጠናከር እና የሪፎርም እና የልማት አጀንዳዎችን በመደገፍ እንዲሁም ንግድና ኢንቨስትመንትን በማሳደግ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ በወሰደችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተመዘገቡ ለውጦችን ያብራሩ ሲሆን ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ያላቸው ጠንካራ የትብብር ማዕቀፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ጄኒ ቻፕማን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የወሰደችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አድንቀው፤ እንግሊዝ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እና የልማት ስራዎችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

BYD ከ115,000 በላይ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጸ

የቻይናው ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪኖች አምራች ቢ.ዋይ.ዲ በዲዛይንና በባትሪ ተከላ...

የትራምፕን ንግግር የህንድ መንግስት ስለ ጉዳዩ ምንም የማዉቀዉ ነገር የለም ብሏል

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሩሲያን ነዳጅ ላለመግዛት መስማማታቸውን...

ከ290 በላይ ሐኪሞች በአጥንት ቀዶ ሕክምና ስፔሻላይዝድ በማድረግ ላይ ናቸው

የአጥንት ቀዶ ሕክምና አገልግሎት አሰጣጥን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማጎልበት...