በትራንስሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ ባለቤትነት የተያዘው ኢንፊኒክስ እና የአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ወጣቱን በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመደገፍ እና አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ጥቅምት 18/2018 አ.ም ተፈራርመዋል ።
የመግባቢያ ስምምነቱም የኢንፊኒክስኒ ክለብን በተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለማቋቋም የሚያስችለው ነው ተብሏል።
በዚህም ተማሪዎቹ በግል እና ሙያዊ እድገት ላይ ያተኮሩ ወርክሾፖች እና የማማከር ፕሮግራሞች ውስጥ እንዲሳተፉ እድል እንደሚሰጥ ተገልጿል ።
እንዲሁም መምህራን የቴክኖሎጂ ስልጠና እንደሚያገኙ ተጠቅሷል።
ስለ ስምምነቱ አስፈላጊነት የገለፁት የአዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ተሰፋዬ አድማሱ “ይህ የመግባቢያ ስምምነት ከጽሑፍ ሰነድ በላይ ነው ብለዋል።
የኮሌጁ ተማሪዎችም ከተግባራዊ ልምድ በተጨማሪ የስራ እድላቸውን እና በራስ መተማመናቸውን የሚያሳድጉበት መሆኑ ተጠቅሷል።
