ኤን. ኤም. ሲ ሪል ስቴት በጋራ ማልማትና መገንባት ስምምነት አድርገው ከነበሩ አልሚዎች ጋር ነው ርክክብ ያደረገው።
ካርታ የተረከቡ ነዋሪዎች ሪል ስቴቱ ቃሉን አክብሮ በመገኘቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ለአቶ መሠረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዶክተር ጫምዶ እንጫሊ ሪል ስቴት በዚህ መልኩ ቃሉን ሲያከብር ደስ ይላል ብለዋል፡፡
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መሠረት መኮንን እንደተናገሩት ዛሬ ነሀሴ 10/2017 በስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የርክክብ ስነስርአት ላይ ከይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በተጨማሪ የቁልፍ ርክክብም ተከናውኗል ብለዋል።ለመላ የድርጅቱ ባልደረቦችም ምስጋና አቅርበዋል።
የኤን. ኤም. ሲ ሪልስቴት ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባቀረበለት ጥሪ መሠረት፤ ለአቅመ-ደካሞችና ለድሀ ድሀ ነዋሪዎች የሚያገለግሉ ቤቶች ሠርቶ ያስረከበ ሲሆን የሸገር ዳቦ ሱቆችን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ በሚገኙ 13ቱም ወረዳዎች እንዲገነባ ማድረጉም የሚታወስ ነው።
ኤን. ኤም. ሲ ሪል ስቴት በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የቤት ችግር ለማቃለል በአቃቂ 11 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በሚገመት ካፒታል 1ሺህ ቤቶችን በመገንባት ላይ እንደሚገኝም አያይዘው ገልፀዋል የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መሠረት መኮንን።
በቀጣይም ነሐሴ 17 2017 ታላላቅ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት የእውቅና እና የ ዋንጫ ስነስርዓት ይደረጋል።
እንዲሁም ለወላጅ አልባ ህጻናትና ለአቅመደካሞች የ ዱቄት፣መኮረኒ፣ ፓስታ እንዲሁም የምግብ ምገባ ይደረጋል፡፡