የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከአለም ባንክና IMF ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ከእስያ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ (ኤ.አይ.አይ.ቢ) ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር አጃይ ቡሻን ፓንዴይ ጋር መምከራቸው ተዘግቧል።
ሚኒስትሩ፣ የልማት አገሮችን ለመደገፍ ዝቅተኛ የወለድ ተመኖችን ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በተጨማሪም ስለሚገነባው አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሜጋ ፕሮጀክት የዝግጅት ውይይት መጀመሩን ገልጸው፣ በተለይም በኢነርጂው ዘርፍ የ AIIB ድጋፍ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ፓንዴይ በበኩላቸው የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ለመሠረተ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
ሁለቱም ወገኖች ትብብራቸውን በማጠናከር፣ በተለይም በትራንስፖርት፣ ኢነርጂና ትስስር ላይ ለሚያተኩሩ የለውጥ አምጪ ፕሮጀክቶች የባንኩን ድጋፍ በፍጥነት በማሰባሰብ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።